ከክፍል ሃያ አምስት
የቀጠለ
የተወደዳችሁ አንባብያን!
በክፍል ሃያ አምስት የ "ቅብአት" እምነትን በተመለከተ
“መልካሙ በየነ” የተባሉ የተዋሕዶ ልጅ፤ ከእነዚሁ የ "ቅብአት"እምነት ተከታዮች ከሆኑት በአንዱ ለተዘጋጀ
"ወልደ አብ" ለተባለው የክህደት መጸሐፍ የሰጡትን፤ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ያስነበቡንን፤ በአስር ክፍሎች የተዘጋጀ
ምላሽ ትልቅ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ስላገኘነው ምንም ሳንጨምርና ሳንቀንስ ባቀረብንላችሁ መሠረት ትልቅ ግንዛቤ እንዳገኛችሁ እንገምታለን፡፡
ለዛሬው “ጌታሁን ደምፀ” የተባሉት የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ መምህር
ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጻፉትንና፤July 29 2016 በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ያስነበኑንን ትምህርት በጣም ጠቃሚ
ሆኖ ስላገኘነው ለእናንተ ለተዋህዶ ልጆች ማካፈል ስለፈለግን፤ ጽሁፉ ለንባብ እንዲመች ከማስተካከል በስተቀር በሃሳቡ ላይ ምንም
ሳንጨምርና ሳንቀንስ አቅርበንላችኋል፡፡ይህ ጽሁፍ አጭር ግን ትልቅ ትምህርት ሰጪ በመሆኑና በተለይም በነሐሴ አንድ ቀን የእመቤታችንን
የእርገቷን መታሰቢያ ጾም ለመጀመር በተዘጋጀንበት ወቅት የተላለፈ መልእክት በመሆኑ ከወዲሁ እራሳችንን እንድናዘጋጅ የሚያበረታታ
ነው፡፡ጾሙን በተገቢው መንገድ ጾመን ከእመቤታችን በረከት እንድናገኝ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን፡፡ አሜን፡፡