ስለ ወልድ ዋሕድ

መግቢያ

በአብ ሥም አምነን አብን ወላዲ ብለን፤ በወልድ  ሥም አምነን ወልድን ተወላዲ ብለን፤ በመንፈስ ቅዱስ  ሥም አምነን መንፈስ ቅዱስን ሠራፂ ብለን ምንም ለአጠይቆ አካላት በሥም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ብንል በአገዛዝ፣ በሥልጣን፣ በመለኮት፣ በህልውና፣ በፈቃድና ይህን በመሰለ ሁሉ አንድ አምላክ ብለን አምነን ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ ይህችን መንፈሳዊ የመወያያ መድረክ እንጀምራለን።

የዚህ መድረክ አዘጋጅ መንፈሳዊ አቋም

እንደ አንዲቷ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፦
  1. አንድ አምላክ በሆኑ በአብ፤ በወልድ፤ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምናለሁ።
  2. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን  አምናለሁ።
  3. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ መሆኗን  አምናለሁ።
  4. የመላእክትን፣ የጻድቃንን፣ የሰማዕታትን በአጠቃላይ የቅዱሳንን ክብርና አማላጅነታቸውንም  አምናለሁ።

ዓላማ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ስርዓትና ትውፊት ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግና እንዲሁም በዘመናችን ቤተ ክርስቲያንን እናደሳለን ብለው በአመጽ የተነሱት የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች በሚያሰራጩት  የክህደት ትምህርታቸው አንዳንድ የዋሃን ምዕመናን  እንዳይሳሳቱ የበኩሌን አስተዋጽኦ ለማበርከት ነው ፡፡

No comments:

Post a Comment