Sunday, August 9, 2015

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ፡፡” ማቴ.7፤15 ክፍል አስር

በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

የተከበራችሁ የዚህ ድረ ገጽ ታዳሚዎች! እንደምን ሰነበታችሁ?
በክፍል ስምንትና በክፍል ዘጠኝ ዘገባችን "ከሐሰተኛው መምህር" ተጠበቁ በሚል ንዑስ ርዕስ ስለ ሰሎሞን ዮሐንስ የምንፍቅና ትምህርት አስነብበናችሁ በይቀጥላል አቆይተነው እንደነበር ይታወሳል፡፡ሆኖም አሁን ባለበት ደብር ምን እየሰራ እንደሆነ ተክክለኛውን ጭብጥ አግኝተን እስከምናቀርብላችሁ ድረስ፤ ለዛሬው ስለ ተሐድሶ መናፍቃን ወቀታዊ የጥፋት እንቅስቃሴ Bini Zelideta የተባሉት የቤ/ክ ልጅ ያዘጋጁትንና በማህበራዊ ድረ ገጽ ያስነበቡንን ጽሁፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ስላገኘነው ምንም ሳንጨምርና ሳነቀንስ አቅርበነዋል፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ከከሃድያንና ከመናፍቃን የስህተት ትምህርት ይጠበቅልን!!!



Bini Zelideta

“ተሃድሶ የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ፈተና”
ጠላት ዲያቢሎስ ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ላይ ያላዘመተው ሠራዊት ፣ ያልሰነዘረው ፈተና አለ ለማለት አይቻልም ፡፡ በየጊዜው ስልቱን እየቀያየረ የሚቃጣባት ፈተና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከረረ መምጣቱ ዲያቢሎስ ጊዜው እንደተፈጸመበት ዐውቆ ያለ የሌለ ኃይሉን በመጠቀም ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡