በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

Bini Zelideta
የተከበራችሁ የዚህ ድረ ገጽ ታዳሚዎች! እንደምን ሰነበታችሁ?
በክፍል ስምንትና በክፍል ዘጠኝ ዘገባችን "ከሐሰተኛው መምህር" ተጠበቁ በሚል ንዑስ ርዕስ ስለ ሰሎሞን ዮሐንስ የምንፍቅና ትምህርት አስነብበናችሁ በይቀጥላል አቆይተነው እንደነበር ይታወሳል፡፡ሆኖም አሁን ባለበት ደብር ምን እየሰራ እንደሆነ ተክክለኛውን ጭብጥ አግኝተን እስከምናቀርብላችሁ ድረስ፤ ለዛሬው ስለ ተሐድሶ መናፍቃን ወቀታዊ የጥፋት እንቅስቃሴ Bini Zelideta የተባሉት የቤ/ክ ልጅ ያዘጋጁትንና በማህበራዊ ድረ ገጽ ያስነበቡንን ጽሁፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ስላገኘነው ምንም ሳንጨምርና ሳነቀንስ አቅርበነዋል፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ከከሃድያንና ከመናፍቃን የስህተት ትምህርት ይጠበቅልን!!!

Bini Zelideta
“ተሃድሶ የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ፈተና”
ጠላት ዲያቢሎስ ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ላይ ያላዘመተው ሠራዊት ፣ ያልሰነዘረው ፈተና አለ ለማለት አይቻልም ፡፡ በየጊዜው ስልቱን እየቀያየረ የሚቃጣባት ፈተና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከረረ መምጣቱ ዲያቢሎስ ጊዜው እንደተፈጸመበት ዐውቆ ያለ የሌለ ኃይሉን በመጠቀም ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡ ገና ከምሥረታዋ ማግሥት ሥደት መከራና እንግልት ከፊቷ የተጋረጠባት ክርስትና በኔሮን ቄሳር ዐዋጅ በክርስቲያኖች ላይ የጅምላ አልቂት ተፈርዶባቸው በሠማዕትነት ያለፉትን ንጹሃን ክርስቲያኖች ቁጥራቸውን ከፈጣሪ በቀር የሚያውቅ የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ካታኮምቡ(ግበበ ምድር) ለመግባት በተገደደችበት በዚያ ዘመን ከምድር በታች በተቆፈሩ ጉድጓዶች ቅዱሳት መጻሕፍትን ደብቀው ባያቆዩልን ኖሮ ክርስትና ዛሬ ምን ሊሆን ይችል እንደነበር ለመገመት አያዳግትም ፡፡ የካታኩምቡ ክርስቲያኖች ዛሬ ላለችው ቤ/ክ ባለውለታዎችም ናቸው፡፡ ዛሬም ድረስ ምድረ ሮማን የቱሪስት መናገሻ ያደረጋት ለክርስቲያኖች ማሰቃያነት ሆን ተብሎ የተሰራው የኮሎሲየም አምፊ ቴአትር፣ስታዲየም በመጀመሪያይቱ ቤ/ክ ክርስቲያኖች ደም የጸና ነው፡፡ ይህ የኮሎሲየም አምፊ ቴአትር ሮማውያን ክርስቲያኖች ሲሰቃዩ እየተመለከቱ እንዲዝናኑበት ሆን ተብሎ የተሠራ ቦታ ሲሆን የአንፆኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ በአሰቃቂ ሁኔታ በአናብስት ተበልቶ ያለፈበት፣የሰርምኔሱ ጳጳስ ቅዱስ ፖሊካርፐስ በእሳት ተቃጥሎ የሞተበት እንዲሁም ዕልፍ አዕላፍ ክርስቲያኖች እንጧፍ የነደደዱበት ቦታ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ፈተናዎች የታጠረችው አንዲቷ ቤ/ክ የመጀመሪያውን መ.ክ.ዘ በዚህ መልኩ ብትሻገርም ቀጣዮቹም ዘመናት ከዚህ የተለዩ አልነበሩም ሥደት ፣ መከራ፣ሥቀይና እንግልቱ ይበልጥ ተባብሶ ዕረፍት አሳጥቷት ቀጠለ፡፡ የሚነግሡት ነገሥታት ሁሉ ዐላውያን(ክፉዎች)ስለነበሩ በክርስቲያኖች ላይ ይሙት በቃ ይፈርዱባቸው ነበር ከእነዚህም ውስጥ ኔሮን ቄሳር፣ድምጥያኖሰ፣ድዮቅልጥያኖስ፣ትራጃን እና አርያኖስ ዋነኞቹ ነገሥታት ነበሩ ይህም እስከ 3ኛው መ.ክ.ዘ የቀጠለ ግዞት ነበር፡፡ ዲያቢሎስ ይህን ሁሉ ፈተና ሰንዝሮባት ሊያጠፋት ባለመቻሉ በ325 ዓ/ም ርጉም አርዮስን አስነሥቶባት ፤ ይልቁንም በ381 እና በ431ዓ/ም መቅደንዮስን እና ንስጥሮስን አዝምቶባት ሊያናውጻት ሞከረ ግን አልተሳካለትም፡፡ ከዚያም በኋላ በ8ኛው፣በ14ኛው እና በ16ኛው መ.ክ.ዘ በዮዲት ጉዲት፣በግራኝ መሐመድ እና በካቶሊክ ሚስዮናውያን ገዳማቷን ለማቃጠል አቢያተ ክርስቲያናቷን ለማፍረስ እና ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የተደረገባት ዘመቻ ቤ/ክ መቼም የማትረሳውን ጠባሳ ጥሎባት አልፏል፡፡ የሲዖል እና የገሃነም ደጆች አይችሉአትም ተብሎ ስለተገባላት ቃል እንጂ እስከዛሬ ድረስ ባልቆየችም ነበር፡፡ ቤ/ክ እስከዛሬ የደረሰባትን ፈተና በቃል ተናግሮ፣በብዕር ጽፎ ለመዝለቅ አይሞከሬ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ጠላት ዲያቢሎስ ቤ/ክ ላይ ጦሩን አዘመተ፣ጭፍሮኑን ላከ፣ቀስቱን ወረወረ፣ዝናሩን ጨረሰ ነገር ግን አላጠፋትም›› ብሎ እንደተናገረ ዘመናትን አልፋ ዛሬ ደርሳለች፡፡
ለመንደርደሪያ ይህን ያህል ካልኩ ወደ ዛሬው ዐቢይ መልዕቴ ላምራችሁ ይህም በኢተዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ላይ የተጀመረው የተሃድሶ መናፍቃን ዘመቻ ነው፡፡ ምንም እንኳ ይህ ዘመቻ በሌሎቹም እህት አቢያተ ክርስቲያናት ላይ ማለትም በግብፅ፣በሶርያ፣በአርመን እና በሕንድ ላይ ተሞክሮ በተወሰኑት ላይ ሠይጣን ድልን ቢቀዳጅም አልሞት ባይ ተጋዳይ ነውና ይህን ሃሳቡን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክን ላይም ለመተግበር በከፍተኛ ሁኔታ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡ በዚህ በያዝነው በ21ኛው መ.ክ.ዘ የተሃድሶ መናፍቃን በቤ/ክ ላይ እያደረጉት ያለው ዘመቻ ከዚህ በፊት ከገጠማት ፈተናዎች ሁሉ እስከፊ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ ዲያቢሎስ ከውጭ ታግሎ መጣል ቢያቅተው ቤተ ክርስቲያንን ከአብራኳ በተገኙ የበሉበትን ወጭት ሰባሪዎች በሆኑ ሥጋውያን ሰዎች መሸርሸሩን ተያይዞታል፡፡ ይህን ዘመቻም አሳሳቢ የሚያደርገው ተሃድሶ መቀመጫውን በኛው ደጀ ሰላም ማድረጉ ነው፡፡ ዛሬ ቤ/ክ ተኩላ ሆኖ ሳለ ቄስ ነኝ ፣ዲያቆን ነኝ እያለ መንጋውን ለማሳሳት በሚፋጠን ትውልድ ተወራለች! ይህ የተጋጋለ ቤተ ክርስቲያንን የመቆናጠጥ አንቅስቃሴ በመናፍቃነ እና በተሃድሶ መናፍቃን ጥምር ጉባዔ የተነደፈ ስልተዊ ዕቅድ ነው፡፡
**የመናፍቃን እና የተሃድሶ መናፍቃን ልዩነት ምንድን ነው?
መናፍቃን የሚባሉት የራሳቸው ስም ያላቸው ፣ ቦታ ከልለው ፣ ሰም አስጸድቀው ፣ የራሳቸውን አዳራሽ ሠርተው የሚተዳደሩ አካላት ናቸው ልክ እንደነ ሙሉ ወንጌል ፣ መሠረተ ክርስቶስ ፣ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት እና የመሳሰሉት ማለት ነው፡፡
**የተሃድሶ መናፍቃን የሚባሉት ደግሞ አንድም የራሳቸው ነገር የሌላቸው ፣ ስማቸውም በመንግሥት ያተመዘገበ እና በኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ስም እራሳቸውን እየወከሉ ግልጽ ምንፍቅናን በመስበክ የዋሃንን ከደጀ ሠላም የሚያስኮበልሉ ሲሆኑ ዋነኛ ዓላማቸውም ምዕመናንን ከቤ/ክ ቀስ በቀስ እያሰስኮበለሉ ለመናፍቃን አዳራሽ መገበር ነው፡፡ መናፍቃን እና የተሃድሶ መናፍቃን የአንድ ሣንቲም ሁለት ግልባጮች ናቸው፡፡ በጣም ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ተሃድሶ ሲባል በተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ እተካሄደ ያለ ስውር ደባ ሳይሆን በጣም ሥር የሰደደና በብዙ ሠራዊት የሚመራ አስጊ አካል መሆኑን ማጤን ያስፈልጋል እንዲህ የሚታሰብ ካለሆነ ግን አደጋው የከፋ ነው ፡፡ ተሃድሶ ከቤተ ክርስቲያናችን የበላይ አካል አነሥቶ እስከ ምዕመናን ዘንድ የሚገኝ የጊዜው አደገኛ አካል ነው ፡፡ ምንም እንኳ በተደጋጋሚ ስለዚህ አጥፊ አካል በየጊዜው ተጨባጭ ማስረጃዎች ቢሰራጩም ዛሬም ድረስ ጥቂት በማይባሉ ኦርቶዶክሳውያን ላይ መደናገርን የፈጠረ ጉዳይ ሆኖአል፡፡ ተሃድሶ የሚባል ነገር ስለመኖሩ የሚጠራጠሩም አልጠፉም፡፡ ሆኖም ከትላነት ዛሬ እጅግ ይሻላል ማለቱ ሳይሻል አይቀርም ምክንያቱም አጥጋቢ በሚባል መልኩ አብዛኛው ምዕመን የተሃድሶን ስውር ደባ ተረድቶታልና፡፡ ለዚህም ግልጽ ማሳያው ትናንት ይህን የተሃድሶ ሴራ ስናጋልጥ ይደርስብን የነበረው የስድብ እና የእርግማን ውርጅብኝ በምርቃት ተቀይሮ ዛሬ ሁሉም አጥፊውን አካል ሲያወግዝ እያየነው ያለው ሃቅ ነውና!! ከራሴ እንኳ ብነሣ ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የተሃድሶ መናፍቃንን ለማጋለጥ ባደረግሁት እንቅስቃሴ የደረሰብኝን ነቀፋ እና በግል ስልኬም ጭምር ተደውሎ የተደረገብኝ የግድያ ዛቻ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን የሚያስደስተው ነገር ትናንት ባለማወቅ እነዚህን የተሃድሶ ምንደኞች ይደግፉ የነበሩ ሰዎች ዛሬ እውነቱን ተረድተው ከግለሰብ ይልቅ ለቤ/ክ ዘብ መቆማቸው ነው፡፡ ለዛሬውም አንዳንድ ምዕመናን እነዚህ ሰዎች ተሃድሶ ስለመሆናቸው ምን ማስረጃ አላችሁ በማለት ለጠየቃችሁኝ ጥያቄ ከራሳቸው (ከተሃድሶ መናፍቃን) አስተምህሮ የተወሰኑትን እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ፡፡ ከዚህ በታች ምትመለከቷቸው እጅግ አሳሳች ትምህርቶች ምዕመናንን ሆን ብሎ ከቤ/ክን ለማስኮብለል ሙዝን በኮሶ ዓይነት የኑፋቄ ትምህርቶች ናቸውና ማስተዋል ይጠይቃሉ፡፡
**የመጀመሪያው ፓስተር ሐዋዝ በራሱ እና ኤሽታኦል በተሰኘው የተሃድሶ መናፍቃን ድረ ገጽ ላይ ከሚያሰራጫቸው ግልጽ ምንፍቅና ትምህርቶች ውስጥ ተሃድሶ ስለመሆኑ እና የተሃድሶን አስፈለጊነት ይህን ብሎአል፡-(ከራሴ አንዳች አልጨመርኩም አሁኑኑ የራሱ ገጽ ላይ በመግባት ማየት ይቻላል)
~~~~## የመታደስ ዘመን !##~~~~~
‹‹እንግዲህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሐ ግቡ፣ከመንገዳችሁም ተመለሱ፣ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል (የሐዋ 3፡19)።
መንፈሳዊ ሕይወት ዕለት ተዕለት እየታደ ሰመሄድይ ገባዋል፡፡ይህ ተሐድሶ የሚመጣው ደግሞ፣ንስሐ በመግባትና ከመንገዳችን በመመለስ ነው፡፡ንስሐ ኃጢአትን የሚደመስስ መንፈሳዊ ኃይል ነው፡፡የመታደስ ዘመን የሚመጣው ኃጢአታችንን ትተን፣ከገዛ መንገዳችንም በንስሐ የተመለስ ንእንደሆነ ነው፡፡ወዳጄሆይ፣የመታደስ ዘመን እንዲመጣልዎ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ኃጢአትን ይተዉ፣ከገዛ መንገድዎም ይመለሱ! በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነውና(1ዮ1፡በኃጢአታችን እንናዘዝ፣ከመንገዳችንም እንመለስ።ይህ ሲሆን ነው፣የመታደስ ዘመን የሚመጣልን፡፡የመታደስ ዘመን ይሁንልዎ!››
በማለት የተሃድሶን አስፈላጊነት ተናግሯል እዚህ ጋር እውነተኛ የቤ/ክንን ትምህርት ተምሮ ያደገ ከዚህ አነጋገር ብዙ ስህተቶችን ነቅሶ ማውጣት ይችላል አውን ይህ የኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ እተምህሮ ነውን? እውን ይህች ዓይነቷ አገላለጽ ከማን ተወረሰች ናት ? ይህን ካለ በኋላ ወረድ ብሎ ‹‹የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው›› ይላል፡፡ እናንተ አመሳጥሩት እኔ ወደ ሁለተኛው የፓስተር ሀዋዝ ት/ት ልለፍ፡-
2ኛ)ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤(በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ)፥ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3 : 13
አዎን መፍጠን ወደ እርሱ ራስ ወደሆነው ጌታ፤መፍጠን እርሱን እንመስል ዘንድ ለተወሰንንበት፤መፍጠን ወደ ኃይማኖታችን ራስ ሊቀካህናት እና ፈፃሚ።በራሳችን ፍፁም እንደሆንን እና ጥግ ላይ እንደደረስን በማሞካሸት ሳይሆን ገና ያልጨረስነው አስገራሚ መለኮታዊ ክብር እንዳለን እያሰብን ወደ እርሱ መዘርጋትን እንውደድ።የዳንበትን እውነት ደግሞ እርሱን ይዘን ከፍ ወዳለው ክብ እና መገለጥ እናድግ ዘንድ ነው።በኋላችን ያለውን እየረሳን ከፊት ያለንን ታላቅ ሽልማት እና ዘለአለማዊ ርስት ጌታ ያዘጋጀልንን እያየን እንደወራሽ እና ተሸላሚ ልንዘረጋ እምነትን በመንፈስ ቅዱስ ልንታጠቅ ይገባናል።ከጀርባችን ካለው ይልቅ ከፊታችን ያለው ጌታ እጅግ ይበልጣል።እርሱ ራዕያችን፤እርሱ መድረሻ ወደባችን፤እርሱ ወደፊታችን፤እርሱ አላማችን ነው።እርሱ ይታየናል ወደ።እርሱ እንዘረጋለን ጀርባችንን ደግሞ ለኋላው ሰጥተናል።ገና ለመውረስ ሳይሆን ስለወረስን ያወረሰንን ጌታ እንከተለዋለን።አልያም ምንሄድበትን አላወቅነውም ማለትነው ? ገና መዳናችንን እንድንጠራጠር እንወርሳለን አንወርስም እያልን ባለንበት እንድንቆዝም አልተጠራንም።ይልቁንስ ከፍከፍ ያለውን ክብር እናገኝ ዘንድ ነው ወደ ተጠራንበት ህይወት መፍጠን ያለብን።ሚያዘገዩን ብዙ አሰናካዬች በዝህች አለም ከፍታ እና ዘውድ ሚመስሉ ቢኖሩም እንሱ ከኋላችን ናቸው።እኛስ መዳናችን የተፈፀመበትን እና የፈፀመልንን የተሰቀለውን ክርስቶስን ፊት ለፊት በማየት ምልክትን እንፈጥናለን የአይን ጥቅሻን እንፈጥናለን።ለምስክርነት እንፈጥናለን ሌላው ጉዳይ ከጀርባችን ነው።ጀርባ አይታይም ጀርባ የሌባው ፍርሃት እና የክፉዎች ምልክት ነው።ጉዳያችን ከፊት ነው እርሱም የምንሰብከው ከሞትም የተነሳው ዳግመኛም የሚመጣው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።የኋላችን ኋላ ነው ፊት ለፊት ወዳለው እንዘረጋለን የያዘንን እኛም እንይዘዋለን እርሱም የእኛ እኛም የእርሱ ነን።እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3 : 20 አሜን ምልክትን እንፈጥናለን ራስ የሆነውን ክርስቶስን አስቀድመን እኛ እንከተላለን።መንገድም ህይወትም እውነትም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ክብር ለስሙ ይሁን።አሜን።ፀጋ ይብዛላችሁ የቃሉ ብርሃን በልባችሁ ይሙላ።ፍጠኑ ከፊታችሁ ታማኙ አለ።እንደ ቀድሞው ከእኔ ባልሆነ በጌታ ፍቅር እወዳችኋለሁ
ዲ/ንሐዋዝ
ሰኔ 3/2007::
‹‹የዚህ ትምህርቱ ጭብጥ››
‹‹ያለፈውን መርሳት›› ሚል ነው ያም ማለት በእመቤታችን በቅድስት ድንግ ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት ማመን ፣በእምነት፣በጸበል፣በመስቀል መታመን፣ጾም፣ጸሎት፣ሥግደት ባለፈው ሕይወት ይቅሩ ካሁን በኋላ ኢየሱስን ብቻ ወደፊት መከተል የሚል ነው፡፡
**ወደ ሌላኛው የተሃድሶ መናፍቃን ትምህርት ልውሰዳችሁ፡፡ ‹‹ኤሽታኦል አድቨርት›› የተሰኘው የነ ፓስተር ሐዋዝ፣ፓስተር አሰግድ ሳህሉ፣ፓስተር በጋሻው እና ሎች መሰል የተሃድሶ አቀንቃኞች የቢዝነስ ምንጭ እና የምንፍቅና ድረ ገጽ እንዲህ ይላል፡-
***~~~+++ የኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ተአምር እና ዓላማው+++~~~**
ዮሐንስ ወንጌል 2:1-11
1 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ 2 ኢየሱስም ደግሞ ደቀመዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። 3 የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት።የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። 4 ኢየሱስም።አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት። 5 እናቱም ለአገልጋዮቹ።የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።6 አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻ ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። 7 ኢየሱስም።ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው።እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው።እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። 8 አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ሰጡትም። 9 አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደመጣ አላወቀም፤ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ። 10 ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው። 11 ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ክብሩንም ገለጠ፥ደቀመዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።ኢየሱስ እነዚህን ሁሉ ታአምራቶች አርጎ ሳለ ጥቅቶቹን ብቻ የተጻፉልን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚ. ልጅ እንደሆነ በማመን የሚገኘውን ደህንነት ለማግኘት ወደሚያስችል እምነት ሊያመጡን እንዲችሉ ነው፡፡አንዳንዴ የጌታን ተአምራቶች ዋና አላማ የሆነውን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ወደሚያስችለው እውነነት ሊመራን በሚችሉ እውነቶች ላ ይከማተኮር ይልቅ ጌታም ተአምራቶቹን ሲፈጽም፣የመጽሀፍ ቅዱስ ጸሀፊዎችም ሲጽፉ ዋና አላማ ያደርጉትን በኢየሱስ ማመንን ትተን በሌሎች ነገሮች ላይ ትኩረት እንሰጣለን፡፡ለእንዲህ አይነቱ ዝንባሌአችን ትልቅ ማስረጃ ሊሆን ከሚችሉ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎች አንዱ ይህ ክፍል ነው፡፡‹‹‹ብዙ ጊዜ ይህን ተአምር የጌታችን የኢሱስ ክርስቶስ እናት ብፅእት ድንግል ማሪያም ሰዎች ከእግዚ. ጋር ባላቸው ግንኑነት ሊኖራት ሰለሚችለው ድርሻ መከራከሪያ አብዝቶ ሲጠቀስ እሰማለሁ›› ፡፡በሌላ ጎኑ ደግሞ አልኮል መጠጣት ይቻላል ወይስ አይቻልም ለሚል ሙግት በማስረጃነት ይጠቃሳል፡፡
ለመሆኑ ኢየሱስ ይህን ተአምራት በመስራቱ የተገኘው ውጤት ምንድን ነበር?
የተአምራቱ አላማ በአጭሩ ክብሩን ለመግለጥ ነው፡፡ዮሀንስ በታሪኩ መጨረሻ ይህንን ነገር በማረጋገጥ " ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ክብሩንም ገለጠ፥ደቀመዛሙርቱም በእርሱ አመኑ" በማለት ጽፎልናል፡፡
ሌላው አስፈላጊ ጥያቄ ክብሩን የገለጠው የት ነው ? የሚል ነው፡፡ጌታ የተአምራቶቹን ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር ለማድረግ፣ በዚያም ውስጥ ማንነቱን ለማሳየት ወደ ነገስታ ትቤት አልሄደም፡፡ነገር ግን ያደሙትን እንግዳ በሚገባ ለማስተናገድ የሚበቃ ነገ ወደሌላቸው ጉድለት ወደአለባቸው ሰዎች ዘንድ ሄደ፡፡‹‹‹አብዛኞቻችን እንደምንገምተው በተለያዩ አዳራሾች ጉባኤዎች በመዘርጋት በተደጋጋሚ ስለምንገናኝ (ስለማንሰበሰብ) " የምትሰበሰቡበት ቦታ ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን አይመስለኝም ሰለዚህ ከእናንተ ጋር ሆኖ እግዚ. ማምለክ ይከብደኛል" የሚሉ ሰዎችም እንዳሉ እሙን ነው›› ጌታ በቃና ዘገሊላ ታሪክ ውስጥ ክብሩን የገለጠበት ቦታ ሰርግ ቤት ነው፡፡ይህ የጋብቻን ክቡርነት የሚያመለክት ብቻ ሳይሆን ጌታ ኢየሱስ በማህበራዊ ግንኙነታችን ውስጥ የተለመዱ በሚመስሉ መገኛኛ ምክንያቶቻችን መሀል ሊገኝ እና ተአምራትን ሊያረግ እንደሚችል ያረጋግጣል፡፡አንዳንዴ በሰርግ ፣በልደት ሥፍራ ላይ ወንጌል በመሰበኩ እንደው እነዚህተ-------ቦታ አይመርጡም፣ ምናለበት አሁን ሰርግ ነው፣ልደት ነው ለቀቅ ቢያደርጉን የሚሉ ሰዎችም አሉ፡፡ጌታ ግን ታላቅና አስገራሚ የሆነውን ተአምራቱን ለዚያውም የመጀመሪያ ተአምራቱን በቃና ዘገሊላ በሰርግ ላይ አደረገ፡፡ጌታ ተአምራቱን ለመስራት፣ የሰውን ጉድለ ትለመሙላት የሚያስፈልገው የቦታው አይነት ሳይሆን በክብር መጋበዙ ነው፡፡እድምተኛችን እናርገው እንጂ እሱይ መጣል፡፡(ይላል)
‹‹የዚህ መልዕክት ዋና ጭብጥ››
1ኛ)በቃና የተፈጸመው ተዓምር በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የተፈጸመ ነው የሚለው አስተምህሮ የተሳሳተ ነው የሚል ሲሆን ሃተታው እንዲህ ይላል ‹‹ብዙ ጊዜ ይህን ተአምር የጌታችን የኢሱስ ክርስቶስ እናት ብፅእት ድንግልማሪያም
ሰዎች ከእግዚ. ጋር ባላቸው ግንኑነት ሊኖራት ሰለሚችለው ድርሻ መከራከሪያ አብዝቶ ሲጠቀስ እሰማለሁ›› የሚለው ቃል ነው ፡፡ 2ኛው) መልዕክት ደግሞ የአዳራሽ ጉባዔ መደረጉ ችግር የለውም የሚል ነው ለዚህም ያቀረቡት ሃተታ፡- ‹‹አብዛኞቻችን እንደምንገምተው በተለያዩ አዳራሾች ጉባኤዎች በመዘርጋት በተደጋጋሚ ስለምንገናኝ (ስለማንሰበሰብ) " የምትሰበሰቡበት ቦታ ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን አይመስለኝም ሰለዚህ ከእናንተ ጋር ሆኖ እግዚ. ማምለክ ይከብደኛል" የሚሉ ሰዎችም እንዳሉ እሙን ነው›› ጌታ በቃና ዘገሊላ ታሪክ ውስጥ ክብሩን የገለጠበት ቦታ ሰርግ ቤት ነው፡፡ይህ የጋብቻን ክቡርነት የሚያመለክት ብቻ ሳይሆን ጌታ ኢየሱስ በማህበራዊ ግንኙነታችን ውስጥ የተለመዱ በሚመስሉ መገኛኛ ምክንያቶቻችን መሀል ሊገኝ እና ተአምራትን ሊያረግ እንደሚችል ያረጋግጣል፡፡
በማለት የትም ሆነን ጌታን ማምለክ እንችላለን የሚል የአዳራሽ ጉባዔን ለማወደስ ሞክረዋል፡፡(በነገራችን ላይ ልብ ብላችሁ ካነባችሁ እግዚአብሔር የሚለውን ሥም ሙሉውን መጻፍ ደብሮአቸው እግዚ. እያሉ ጎራርደውታል ከላይ በደንብ እዩት ፤ ይህ ነው እንግዲህ የእነርሱ ኃይማኖት ምሥጢረ ሥላሴን መቃማቸውን ተመልከቱ ‹‹እግዚአብሔር ማለት የሦስቱ ፍጹማን አካላት መጠሪያ ስም ነው(የአብ፣የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ) እነርሱ ግን እግዚ. በማለት አድሰውታል ከዚህ በላይ ተሃድሶ የት አለ?)
***ቀጣዩ ማስረጃዬ ደግሞ ፓስተር በጋሻው ደሳለኝ በቅርቡ ባወጣው "የሚንከራተቱ ከዋክብት" የተሰኘ መጽሐፉ ላይ ያሰፈረውን ግልጽ ስድብ እና ኑፋቄ ሆናል እንዲህ ይላል፡-
‹‹በዚህ ዘመ የቤክ ጉልበት የጨረሰዉ በዉሀ ዉስጥ እንደሚሮጥ ሰዉ አይነት ሩጫ ዋጋ እያስከፈለ ያለዉ ታላቁ ጥፋት ልዩ ልዩ የሆነ የሀሰት ትምህርት ነዉ።ብዙ ጊዜ መፅሀፍ ቅዱስ በፍፁም የማይደግፈዉ የስህተት ትምህርት በጆሯችን ሰምተን ይሆናል።ብዙም የሚያስቁና የሚያስገርሙ ተረት መሰል አገልግሎቶች ላይ ተካፍለን ይሆናል።ከእንግዲህ ግን ከዚህ ፈቀቅ እንበል፣በዘለአለማችን ላ ይእንዲቀልዱበት አንፍቀድላቸዉ።በማለት የኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ አስተምህሮ ስህተት መሆኑን እና ገድላት እና ድርሳናትን በሽሙጥ ‹‹የሚያስቁ.... የሚያስገርሙ.... ተረት... ›› በማለት ከዚሀ ፈቀቅ እንበል ይለናል ፣ ይልቁንም በዘለዓለማችን ላይ አንዲቀልዱበት አንፍቀድላቸው በማለት እኛ ኦርቶዶክሳውያንን በግልጽ ነቅፎናል እውን በጋሻው ተሃድሶ አይደለምን? እርሱ የፈለፈላቸውስ ተሃድሶ አይደሉምን? ከዚህ በኋላ እዚህን ሰዎች መከተል እና ስለ እነርሱ መከራከር አራሱ ተሃድሶ መሆን ነው ከሰው ይልቅ ለቤ/ክ ዘብ እንቁም!!!(በነገራችን ላይ የሚንከራተቱ ከዋክብት ያላቸው ምዕመናንን ነው ምክንያቱም በቤ/ክ አጠራራር ከዋክብተ ቤ/ክ የሚባሉት ማዕመናን ናቸውና እርሱ ግን ይህንን እንደ አርዮስ የራሱን ትርጉም በመስጠት የሚያመልኩትን እንደማያውቁ ሰዎች የሚንከራተቱ ብሎ ገለጸን እናመሰግናለን ፓስተር ሌላም ካለ ይስደቡን!)፡፡
***ስለ ፓስተር አሰግድ ሳህሉም ከጠየቅኸኝ ከ40 በላይ በተከታታይ ከለቀቀቃቸው ትምህርቶች ውስጥ አንድም ቀን ነገረ ማርያም እና ነገረ ቅዱሳንን ሳይሰብክ ለወራት ያህል ቃለ ዐዋዲ በተሰኘው የግል መፈንጫ ጣቢያው ላይ በኦርቶዶክስ ስም እየነገደ ይገኛል፡፡ እንደ ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ አስተምህሮ አንድ ሰባኪ አንድ ደቂቃ እንኳ ቢያስተምር በዚያች ጊዜ ውስጥ ነገረ መለኮትን፣ነገረ ማርያምን እና ነገረ ቅዱሳንን አካቶ መስበክ አለበት፡፡ እርሱ ግን የድንግል እናታችንን እና የቅዱሳንን ስም መግቢያና መደምደሚያ ላይ እንኳ መጥራት ከብዶት ተስተውሏል ምክንያቱም የእርሱ ብቸኛ መልዕከት ‹‹ኢየሱስ..ኢየሱስ ብቻ›› ነው ቤ/ክ ደግሞ ‹‹ብቸኛ›› የሚል አስተምህሮ የላትም ይሄ የሙሉ ወንጌል ትምህርት ነው!!!
***ሌላኛው ደግሞ ደቂቀ አሰግድ ሳህሉ በቅርቡ ቃለ ዐዋዲ በተሰኘው ብቸኛው መተንፈሻቸው ላይ ‹‹የምንጾመው ስለዳንን ነው›› በማለት ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ትምህርት ሰጥቷል፡፡ እውነት ስለዳንን ነው የምንጾመው? ወይስ ለመዳን ነው የምንጾመው? ከዳንንማ ለምን እንጾማለን? በእርግጥ መናፍቅ ስለሆነ አንዴ በጸጋው ድነናል ለማለት ፈልጎ ሊሆን ይችላል ሆኖም ይህ ትምህርት የፕሮቴስታንቱ ዓለም አስተምህሮ እንጂ የኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ አይደለም !!! እኛ የዳነው እኮ ከውርስ ኃጢአት ነው! እንዲያው ክርስቶስ ስለሞተልን ብቻ አንዴ ሞቶልናል ብለን በቀጥታ ገነት አንገባም እኮ! ምክንያቱም ጾም፣ጸሎት፣ሥግደት፣ምጽዋት፣አሥራት በኩራት፣ንሰሃ እንዲሁም የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም በመቀበል ተጨማሪ ትሩፋቶችን መከወን ግድ ይለናልና፡፡ አለበለዚያማ እራሱ ባለቤቱ ጹሙ ጸልዩ በላለንም ነበር! እባካችሁ እነዚህን ሰዎች በየዋህነት የምትከተሉ ሰዎች ጥቂት ቆም ብላችሁ አስቡ አልያም ስለምን እያስተማሩ እንደሆነ መርምሩ እንዲያው በየአዳራሹ እየተከተልናቸው አብረን እንዳንጠፋ እናስተውል! እነዚህ ሁሉም ቀናቸውን ጠብቀው ያልፋሉ ቤ/ክ ግን ዘለዓለማዊት ናትና እርሷን እንከተል፡፡ አምላከ ቅዱሳን የድንግል ልጅ መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ አጽራረ ቤ/ክንን ያስታግስልን፡፡ (ስለ ተሃድሶ መናፍቃን መረጃው ገና ይቀጥላል)፡፡
እነዚህን አባባሎች ላስከትልና መልዕክቴን እቋጫለሁ፡-
+ ተሃድሶ የለም ማለት ኤች አይ ቪ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም እንደማለት ነው፡፡ (መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ)
+ ተሃድሶ የለም ማለት ለተሃድሶ መኖር ማረጋገጫ ነው፡፡ (ዲያቆን ዓባይነህ ካሴ ዘማኅበረ ቅዱሳን)
+ ተሃድሶ ማለት ነፍሳትን ለፕሮቴስታንት የሚገብር ገባር ወንዝ ማለት ነው፡፡ (ሊቀ ጉባዔ ጌታሁን)
ቢኒ ዘልደታ
ሰኔ 09/2007 ዓ/ም፡፡

No comments:
Post a Comment