Sunday, December 13, 2015

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ፡፡” ማቴ.7፤15 ክፍል አስራ ሦስት

ከቁጥር አስራ ሁለት የቀጠለ

የተወደዳችሁ አንባብያን!
እንደምን ሰነበታችሁ ?

‹‹ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ›› በሚለው ዐቢይ ርዕስ ሥር፤ በክፍል አስራ አንድና አስራ ሁለት ላይ ወቅታዊ የሆነውን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የውስጥና የውጪ መናፍቃን/ተሐድሶዎች/ ችግር በማስመልከት ማህበረ ቅዱሳን በድረ-ገጹ (www.eotcmk.org) ያቀረበውን ዘገባ ተመልክታችሁ ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኛችሁ በመገመት፤በመቀጠል ደግሞ "የተሐድሶ መረብ አድማስና የትኩረት አቅጣጫ" "ንቁ ሳይሆን ተናነቁ" "መንፈሳዊ ኮሌጆችና ደቀ መዛሙርቱ ምንና ምን ናቸው?" በሚሉት ርዕሶች ከማህበረ ቅዱሳን ያገኘነውን በማስረጃ የተደገፈ ዘገባ እነሆ ብለናል፡፡ 

ማስገንዘቢያ፤

የተከበራችሁ አንባብያን የቤተ ክርስቲያን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር አስቀድሞ በቅዱስ ወንጌል እንዲሁም በየጊዜው ደግሞ በተለያየ መንገድ የሚናገረን እራሳችንንም ሆነ ሌላውን ከስህተት ጎዳና እንድንጠብቅ ነው፡፡ስለሆነም እያንዳንዳችን የቤ/ክ ልጆች "ከእኔ ምን ይጠበቃል?"ብለን በመጠየቅ የቤ/ክ እምነት፣ሥርዓትና ትውፊት ከአባቶቻችን በተረከብነው መሠረት እንዲቀጥል ለማድረግ በጾምና በጸሎት ከመታገዝ ጋር አቅማችን የሚችለውን ሁሉ በማድረግ መንፈሳዊ ግዴታችንን እንድንወጣ በቅዱሳን አምላክ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡

መልካም ንባብ!
የተሐድሶ መረብ አድማስና የትኩረት አቅጣጫዎች

ኅዳር 2 ቀን 2008 ዓ.ም
ክፍል ሦስት
ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጽሑፎች ተሐድሶ መናፍቃን በምን ዐይነት መንገድ ምእመናንን እየነጠቁ እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ ከዚህ ቀጥለን በምናወጣቸው ተከታታይ ጽሑፎች ደግሞ የተሐድሶ አድማሱ የት ድረስ እንደሆነ ለአንባቢያን ግንዛቤ የሚሰጥ መረጃ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

የተሐድሶ እንቅስቃሴ ዓለም አቀፋዊ መልክ ያለውና በዓለም ላይ ባሉ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ላይ በፕሮቴስታንት የእምነት ተቋማት የተቃጣ ስውር ሴራ ነው፡፡ እንቅስቃሴው ከውጪ ወደ አገር ውስጥ የመጣ ስለሆነ የተሐድሶው አቀንቃኞች በአሳብ፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ ወዘተ ከሚያግዟቸው በልማት ስም ከተቋቋሙ ድርጅቶች ጋር ከፍተኛ ቁርኝት አላቸው፡፡ ከእነዚህ ድርጅቶች እና ከፕሮቴስታንት ቸርቾች በሚበጀት በጀት፣ ከአገር ውስጥ እስከ ውጪ አገር በተዘረጋ መዋቅር፣ ቤተ ክርስቲያንን ከተቻለ ሙሉ በሙሉ ለመረከብ ፕሮቴስታንት ለማድረግ ካልሆነም ለሁለት ለመክፈል በሚያስችል ስልት እየሠሩ እንደሆነም ተመልክተናል፡፡

በአገር ውስጥ ያሉት ሠላሳ የሚደርሱ የተሐድሶ ማኅበራት የቤተ ክርስቲያን ምንጮች በሆኑት የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ ገዳማት፣ መንፈሳዊ ኮሌጆች፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶችና ማኅበራት ላይ እንዲሁም መዋቅራዊ ድጋፍ ለማግኘት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ ይሠራሉ፡፡ የተለያዩ መመዘኛዎችን በመጠቀም ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ መነሻቸውን አዲስ አበባ ላይ አድርገው በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ሰፋ ያለ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ዕትም ጀምሮ በተከታታይ ጽሑፎች ከመነሻቸው ከአዲስ አበባ ጀምረን ትኩረት ሰጥተው በሚሠሩባቸው አካባቢዎች ያለውን እንቅስቃሴ እንመለከታለን፡፡

አዲስ አበባን ማእከል ያደረገው የተሐድሶ መረብ
አዲስ አበባ የተሐድሶ እንቅስቃሴው ማእከል ነው፡፡ ታሪክ የሚነግረን ተሐድሶዎች እንቅስቀሴው ሲጀመር ጀምሮ ማእከላቸውን አዲስ አበባ አድርገው ወደ ሌሎቹ የአገራችን ክፍሎች ኑፋቄያቸውን ያስፋፉት መሆኑን ነው፡፡ አዲስ አበባ ተሐድሶዎች በየአጥቢያው ተወካዮችን አስገብተው ብዙ ሥራ የሚሠሩበት፣ የተለያዩ የሥልጠና መስጫ ተቋማትን እና ኮሌጆችን ያቋቋሙበት፣ የቤት ለቤት ሥራዎችን በሰፊው የሚሠሩበት፣ የጽዋ ማኅበራትን በብዛት የፈጠሩበት፣ ከክፍለ ሀገር ለሚያመጧቸው ካህናትና ዲያቆናት ሥልጠና የሚሰጡበት ነው፡፡ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር የሚያስተላልፉት፣ አብዛኛው የተሐድሶ መናፍቃን መጻሕፍት የሚታተሙት፣ የገንዘብ ልገሳ የሚያደርጉላ ቸው የመናፍቃን ድርጅቶች የሚገኙት አዲስ አበባ ነው፡፡ ፕሮቴስታንታዊ የአምልኮ ሥርዓት የሚፈጸምባቸው የተሐድሶ አዳራሾች በስፋት የሚገኙትም እዚሁ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የሚያስችላቸውን መዋቅራቸውን የዘረጉትና ስልታቸውን የነደፉት አዲስ አበባን ማእከል አደርገው ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከአዲስ አበባ እየተነሡ ያልደረሱበት የአገራችን ክፍል የለም ማለት ይቻላል፡፡ አዲስ አበባ ላይ ያላቸው መረብም ጠንካራና ሁሉንም አጥቢያዎች የሚያቅፍ ለማድረግ እንቅልፍ አጥተው በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ መሐል አዲስ አበባ አካባቢ ካሉት አጥቢያዎች ተነቅቶባቸው ሲባረሩ በአዲስ አበባ ዙሪያ ወደሚገኙ አጥቢያዎች በመሔድ ተመሳስለው ገብተው የቅሰጣ ሥራቸውን ይሠራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ተልእኳቸውን ተረድታ በውግዘት የለየቻቸውና አጋልጣ ምእመናን እንዲያውቋቸው ያደረገቻቸው ተሐድሶዎች ከጀርባ ሆነው በየአጥቢያው የሰገሰጓቸው ተሐድሶ መናፍቃን ተልእኳቸውን ያፋጥኑላቸዋል፡፡

እንቅስቃሴው በግልም በቡድንም እንዲሁም በድርጅት ስም የሚካሔድ ነው፡፡ በግለሰብ ደረጃ የተሐድሶ አቀንቃኞችን እገሌ ወእገሌ ማለቱ ባያቅትም ለአንባቢም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ጥቅም ካለመኖሩና እነርሱንም የበለጠ እንዲደበቁ ዕድል መስጠት ስለሚሆን ይህንን መጠበቅ የለብንም፡፡ ነገር ግን በብዙ ቦታዎች እንደሚታየው በዓላማ እንቅስቃሴውን የሚመራው አካል አንድ ወይም ጥቂት ነው፡፡ ሌላው ግን ምን እየተሠራ እንደሆነ እንኳን ሳያውቅ ሌሎቹ ስለሔዱ ብቻ የሚከተል ነው፡፡

በተደጋጋሚ ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ካህናትን እያመጡ አዲስ አበባ ላይ ያሠለጥናሉ፡፡ በተለይ ከገጠር ለሥልጠና የሚያመጧቸው ካህናት ከጥቂቶቹ በስተቀር በየዋህነት ጉዳዩ ምን እንደሆነ ሳይረዱ የሚመጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ ሴራዎች ያውም የቤተ ክርስቲያን ምንጮች ያልናቸው አብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት ላይ ሓላፊነት ላላቸው ሰዎች ተሰጥቶ የፈለጉት ነገር አለመሳካቱን ስናይ የእግዚአብሔርን ጠብቆት እናደንቃለን፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የሚሰጡት ሥልጠና ውጤት ማምጣት ያልቻለው በአንድ በኩል ከሠልጣኞች አቅም ማነስ የተነሣ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የሚከተሉት ዓላማ የጥፋት በመሆኑ እግዚአብሔር እንዳይሳካላቸው ቤተ ክርስቲያንንና ምእመናንን በረድኤት ስለሚጠብቃቸው ነው ብለን እናምናለን፡፡ ተሐድሶዎችም ምዕራባውያን ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ ስውር ተልእኳቸውን ለማሳካት የበጀቱት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንዳይቀርባቸው እንጂ ለጽድቅ ስለ ማይሠሩ ለሪፖርት ብቻ ሥልጠና ሰጥተው የሚልኳቸው ብዙዎችን ነው፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መቦርቦርን እንጀራ ማብሰያ አድርገው የያዙት ብዙ የተሐድሶ ድርጅት አንቀሳቃሾች መናሃሪያቸው አዲስ አበባ ነው፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የተወገዙና ከሥልጣነ ክህነታቸው የተሻሩ ግለሰቦች ሳይቀሩ የክህነት ስማቸውን ተጠቅመው ዲያቆን፣ መሪ ጌታ እያሉ መጻሕፍት ያሳትማሉ፡፡ ሥልጠና የሚሰጡባቸው፣ ኑፋቄያቸውን የሚዘሩባቸው፣ በእነርሱ አነጋገር አምልኮት የሚፈጽሙባቸው፣ በሥውር ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ ሴራ የሚጠነስሱባቸው፣ የቴቪዥን መርሐ ግብራትን የሚቀርጹባቸው፣ የግልና የኪራይ አዳራሾች አሏቸው፡፡ በእነዚህ አዳራሾች ሲያሻቸው ያስጨፍራሉ፣ ሲያሻቸው እንፈውሳለን ይላሉ፣ ሲያሻቸው ደግሞ እነርሱ ሳይማሩና የያዙት ወንጌል ሳይገባቸው ያስተምራሉ፡፡

የቤት ለቤት ቅሰጣ አልበቃ ብሏቸው በመገናኛ ብዙኀን ወደ ሕዝብ መድረስ ጀምረዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ምእመናን ስለ ተሐድሶ ያላቸው ግንዛቤ እየጨመረ መምጣቱ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ከተሐድሶዎች ጋር እያደረጉት ያለው ትንቅንቅ መጎልበቱና ለምእመናን የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብራት እየበረከቱ መምጣታቸው ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም፤ አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ከተሐድሶዎች እጅ ነፃ ለማድረግ ግን ሰፋ ያለና የተቀናጀ ሥራ የሚጠይቅ ነው፡፡

አጥቢያቸው የሚገኘውን ሰንበት ትምህርት ቤት አፍርሰው ሌላ ሰንበት ትምህርት ቤት ለማቋቋም፣ አባላቱን ለሁለት ከፍለው አገልግሎቱ እንዳይካሔድ ለማድረግ የሚጥሩ ከተሐድሶ በሚገኝ ገንዘብ የሚደለሉ አንዳንድ አስተዳዳሪዎችና የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ዓላማችንን ያስፈጽሙልናል ያሏቸውን የሰንበት ተማሪዎች ሰብስበው የተለየ ትምህርት ካስተማሩ በኋላ ተልእኮ ሰጥተው ተመልሰው ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርጉ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሌላ ተልእኮ ይዘው ተመሳስለው የገቡትን የጥፋት መልእክተኞች አካሔድ አጢነው ሲያግዷቸው ለምን ታገዱ ብለው ሰንበት ትምህርት ቤቱን ለመዝጋት የሚነሡ የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች እየበዙ መጥተዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው ምን ያህል ተመሳስለው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደገቡ ነው፡፡ ምእመናንም ሆኑ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች እንዲህ ዓይነት የጥፋት ተልእኮ አንግበው የሚንቀሳቀሱትን ወገኖች ሲመለከቱ ማንነታቸውን የሚያሳይ መረጃ መሰብሰብ፣ ከማን ጋር እንደሚውሉ፣ ምን እንደሚሠሩ፣ አነጋገራቸው፣ አካሔዳቸው፣ ኦርቶዶክሳዊነታቸው ምን እንደሚመስል ማጣራት ይኖርባቸዋል፡፡

በአንዳንድ አጥቢያዎች ገድላትና ድርሳናት፣ ተአምረ ማርያምና ስንክሳር እንዳይነበቡ የሚከለክሉ አስተዳዳሪዎች አሉ፡፡ የጠበል ቦታ አያስፈልግም ብለው ለጋራዥ በማከራየት ገንዘብ ከመመዝበር አልፈው ምእመናንን ከድኅነት የሚለዩና የተሐድሶ አጋርነታቸውን የሚገልጡ ወገኖች አሉ፡፡ ተሐድሶዎቹ ከእንደዚህ ያሉ የጫኑዋቸውን ተሸክመው ለማስፈጸም ከሚደክሙ አካላት ጋር በመመሳጠር ዐውደ ምሕረትን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ነገር ግን በሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና በጠንካራ ምእመናን ተጋድሎ ዓላማቸው አልተሳካም፡፡ ሰባክያነ ወንጌልን የሚመድቡትና የማስተማር ሓላፊነት የተሰጣቸው አንዳንድ የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች በዐውደ ምሕረት ላይ ወጥተው ሲያስተምሩ ስለ ቅዱሳን ማስተማር የኢየሱስን ማዳን ይሸፍናል ሲሉ ይሰማሉ፡፡ የሚጋብዟቸው መምህራን ደግሞ ኢየሱስን ብቻ እንሰብካለን የሚል መፈክር አንግበው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች ያልገባቸው ወይም አውቀው ለማደናገር የሚጥሩት ስለ ቅዱሳን መስበክ ስለኢየሱስ ክርስቶስ መስበክ መሆኑን ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአንዳንድ አጥቢያዎች አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት ተጀምረው ሳይጠናቀቁ ገና በመቃኞ እያሉ እና አጸዱ እንኳን ቅጥር ሳይኖረው ሁሉም ቁሳቁስ የተሟላለት ዘመናዊ አዳራሽ የሚሠሩም አሉ፡፡ ለምን ተብለው ሲጠየቁ ለወንጌል ቅድሚያ መስጠት ተገቢ ስለሆነ የሚል መልስ ያቀርባሉ፡፡ በእውነቱ የሰው ልጅ ድኅነት ማግኘት ገድዷቸው ይህን ቢያደርጉ መልካም ነበር፡፡ የእነሱ ዓላማ ግን ሌላ ነው፡፡ ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት በአፍአ እንዲቀሩ ማድረግ፡፡ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን አሳንሶ አዳራሾችን ዘመናዊ አድርጐ መገንባት የተሐድሶዎች አንድ ስልት ተደርጎ እየተሠራበት ነው፡፡ ይህንን አካሔድ የሚቃወሙትንየወንጌል ጸሮች እያሉ ይሳደባሉ፤ ምእመናን እንዲጠሏቸው ያደርጋሉ፡፡ ለአካሔዳቸው እንቅፋት ይሆናሉ ያሉዋቸውን በሓላፊነት የሚገኙ አገልጋዮች ማባረር፣ ያላጠፉትን ይህን ጥፋት ፈጸሙ በማለት የሀሰት ስም መስጠት፣ ማብልጠልና ከምእመናን ጋር ማጋጨት በአዲስ አበባ የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ በዚህ ምክንያትም በየፖሊስ ጣቢያውና በየፍርድ ቤቱ ሲጓተቱ የሚውሉ አገልጋዮች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መጥቷል፡፡

ይህ አካሔድ በቶሎ መፍትሔ ካልተሰጠው ከቅዳሴ በኋላ ዐውደ ምሕረት ላይ ተአምረ ማርያም ሳይነበብ ምእመናን ወደ አዳራሽ እንዲገቡ መደረጉ የማይቀር ነው፡፡ እነዚህ እና የመሳሰሉት አስተዳደራዊ ጉዳዮች ሽፋን ተደርገው የሚሠሩ የተሐድሶ ቅሰጣዎች ናቸው፡፡

ሌላው ደግሞ በግልጽ የሚሠራው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፍል ውኃ አካባቢ የሚገኝ ተስፋ ተሐድሶ የሚባል ድርጅት አለ፡፡ ይህ ድርጅት ላለፉት ሦስትና ዐራት ዓመታት ከተለያዩ ቦታዎች ለተውጣጡ የገዳማት አበምኔቶች፣ የአብነት ትምህርት ቤት መምህራን፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለሚያገለግሉ ቀሳውስትና ዲያቆናት ሥልጠና እየሰጠ በሰርተፊኬት አስመርቋል፡፡ ከ፳፻ወ፮ ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ፍኖተ ሕይወት ማኅበረ መድኀኔዓለም የተስፋ ተሐድሶ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት የሚባል ተቋም ከፍቶ በዲፕሎማ ማስመረቅ ጀምሯል፡፡ ድርጅቱ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፳፻ወ፮ ዓ.ም ደግሞ Integrated Theological Training and Skill Development for Africa ከሚባል ኮሌጅ ጋር በመተባበር የመጀመሪያ ዙር ዐሥር ተማሪዎችን በዲፕሎማ አስመርቋል፡፡

በአጠቃላይ የአዲስ አበባ እና ዙሪያውን እንቅስቃሴ ስንመለከት በገንዘብ ጥማት ልቡናቸው በታወረ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ በተሐድሶ እንቅስቀሴ መረብ ውስጥ ባሉ ስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች እና በፕሮቴስታንት ድርጅቶች ጥምረት የሚካሔድ ነው፡፡ ገንዘብ እስካገኙ ድረስ ለቤተ ክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ደንታ የሌላቸው የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ባሉባቸው አጥቢያዎች እና ከተሐድሶዎች ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያላቸው የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች ባሉባቸው አጥቢያዎች ዐውደ ምሕረቱ የሚፈቀደው ለኦርቶዶክሳውያን ሳይሆን ለተሐድሶ መናፍቃን ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያለው እንቅስቃሴ በዚህ መልክ የሚቀጥል ከሆነ ከጊዜ በኋላ የተወሰኑ አጥቢያዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አይደለንም ማለታቸው የማይቀር ነው፡፡
ሰሜኑን ማእከል ያደረገ የተሐድሶ እንቅስቃሴ
ይህ እንቅስቃሴ የክርስትና መሠረት የተጣለበትን ሰሜኑን የአገራችንን ክፍል ለማጥፋት ታቅዶ የሚካሔድ ነው፡፡ እንቅስቃሴው ጥንታውያን ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በትምህርት ስም፣ በማኅበራዊ ልማቶች ስም፣ በእርቅና ሰላም ስም፣ ማረሚያ ቤቶችን እናግዛለን በሚል ስም ምእመናን እና ሕፃናት ላይ ትኩረት አድርገው ይሠራሉ፡፡ የዚህ እንቅስቃሴ ፊታውራሪዎች ከሣቴ ብርሃን የተሐድሶ ድርጅት፣ መሠረተ ክርስቶስ ቸርችና የኢትዮጵያ አዲስ ኪዳን መጥምቃዊት ቸርች ሲሆኑ በግለሰብ ደረጃ እንቅስቃሴው ውስጥ ታላቅ ሱታፌ ያላቸው ግለሰቦች አሉ፡፡

ከሣቴ ብርሃን ከመወገዙ በፊትም የትኩረት አቅጣጫው የነበረው ሰሜኑ የአገራችን ክፍል ነበር፡፡ የከሣቴ ብርሃን ቅጥረኞቹ ጽጌ ሥጦታው፣ ሠረቀ ብርሃን ዘወንጌል፣ ጌታቸው ምትኩ፣ ባዩ ታደሰና ሙሴ መንበሩ ከአዲስ አበባ ተነሥተው በጎጃም በር ወጥተው ሥልጠና ሰጥተው፣ ቅኝት አድርገውና አዳዲስ ተከታዮች አፍርተው በሸዋ በር ይመለሳሉ፡፡ በ፳፻ወ፯ ዓ.ም ብቻ ሸኖ፣ አንጾኪያ፣ ደሴ፣ ጎንደር፣ ባሕር ዳር ሁለት ጊዜ እና አዲስ አበባ ላይ ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናትና አብነት ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ በአጠቃላይ ከሁለት መቶ በላይ ለሚሆኑ ካህናትና የአብነት መምህራን ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ ሥልጠናውን የሚወስዱት ሰዎች የሚመለመሉት በከሣቴ ብርሃን ቢሆንም ሥልጠናው የሚሰጠው በፕሮቴስታንት አዳራሾችና በፕሮቴስታንት ፓስተሮችም ነው፡፡

ከ፳፻ወ፭ ዓ.ም ጀምሮ ብሔራዊ ተሐድሶን አመጣለሁ እያለ ሌሎችን የተሐድሶ ድርጅቶች ሲቀሰቅስና ሲያስተባብር የነበረው ይኸው ድርጅት ባለፈው ዓመት የወንጌል አገልግሎት ማኅበራት ኅብረት የሚባለው እናት የተሐድሶ ድርጅት እንዲቋቋም አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው፡፡ ስሙን በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ስም ሠይሞ ስለሚንቀሳቀስ የቤተ ክርስቲያን አካል መስሎ የሚታያቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ያለ ቤተ ክርስቲያን ዕውቅናና ፈቃድ ከተከፈቱት የቴሌቪዥን መርሐ ግብሮች በተጨማሪ ፳፻ወ፬ ዓ.ም ላይ የተወገዘው ከሣቴ ብርሃን የተሐድሶ ድርጅትም መጥቅዕ የተባለ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ሊጀምር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ሁለተኛው የሰሜኑ የአገራችን ክፍል የተሐድሶ እንቅስቃሴ ፊታውራሪ የሆነችው መሠረተ ክርስቶስ ቸርች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰሜኑን በወንጌል እንወርሳለን የሚል ፕሮጀክት ነድፋ እየሠራች ሲሆን ፕሮጀክቱ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ፈሰስ እየተደረገ የሚሠራ ነው፡፡ መሠረተ ክርስቶስ እንደሽፋን ተጠቅማ ሰሜኑ ላይ ትኩረት አድርጋ የምትሠራው ሁለት ፕሮጀክቶችን ነው፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች ሰሜኑን በወንጌልና የማረሚያ ቤቶች አገልግሎት የሚባሉ ናቸው፡፡ የእነዚህ ፕሮጀክቶች ዋና የትኩረት አቅጣጫ ሰሜኑ የአገራችን ክፍል ቢሆንም በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ እንቅስቀሴዎችን ታደርጋለች፡፡

ሰሜኑን በወንጌል የሚባለው ፕሮጀክት በትግራይ፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ጎጃምና ሸዋ አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ እያደረገች ነው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የተለያዩ አጥቢዎች፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችና ማረሚያ ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሠራች ነው፡፡ ለዚህ ዓላማ ማስፈጸሚያ የሚሆን ገንዘብ የምታገኘው ከተለያዩ የውጪ ድርጅቶች (የፕሮቴስታንት) ከሚላክ ገንዘብ፣ በሚያውቋቸው ሰዎች ከውጪ ከሚሰበሰብ እርዳታ እና ያሠለጠኗቸውን ሰዎች በቪሲዲ በመቅረፅና እርሱን በማሳየት ከደጋፊ ዎች በሚገኝ ገንዘብ ነው፡፡ የመሠረተ ክርስቶስ የልማት ድርጅት (Meserete Kirstos Church Relief Development) የታላቁ ተልእኮ አገልግሎት አጋር ስለሆነ ከዚህ ድርጅትም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ይደረግላታል፡፡

የዚህ እንቅስቃሴ ዓላማ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ካህናት፣ ዲያቆናትና መሪጌቶች በገንዘብ በማታለል፣ የተለያዩ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት፣ ማንነታቸውን መለወጣቸው እንኳን ሳይታወቃቸው የተሐድሶ እንቅስቃሴው አጋርና ቀኝ እጅ እንዲሆኑ በማድረግ በውስጥ ሆነው የተሐድሶ ሥራ እንዲሠሩ ተልእኮ መስጠት ነው፡፡ ሥልጠና የሚሰጡላቸው ደግሞ የተሐድሶውን እንቅስቃሴ ዓላማ ብለው የያዙት እነ ሠረቀ ብርሃን ዘወንጌል፣ ጽጌ ሥጦታው፣ አግዛቸው ተፈራ፣ የዕድል ፈንታ፣ ታምራት፣ ፓ/ር ሰሎሞን ከበደ፣ ወዘተ ናቸው፡፡

በ፳፻፮ ዓ.ም ብቻ ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ለመጡ ከሃምሳ በላይ ለሚሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወረዳ ቤተ ክህነት፣ ሊቃነ ካህናት፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ሥልጠና ሰጥታለች፡፡ ሥልጠናው በተለያዩ ዙሮች መሐል ሜዳ፣ አዲስ አበባና ደብረ ዘይት ላይ የተካሔደ ነበር፡፡ ስለ እርቅና ሰላም አስተምራለሁ በሚል ሰበብ የማሠልጠኛ ሰነድ አዘጋጅታ የራሷን ዶክትሪን እያስተማረች ነው፡፡ ለዚሁ ዓላማ በ፳፻ወ፯ ዓ.ም የብርሃን ፍሬ የሚባል የበጎ አድራጎት ድርጅት አቋቁማለች፡፡ የበጎ አድራጎቱ መመሥረት ዋና ዓላማ በልማት ስም ምንፍቅናን ማስፋፋት ሲሆን “ወንጌልን ማስፋፋት ዋና ዓላማችን ቢሆንም በውስጠ ታዋቂነት የሚሠራ እንጂ ከመተዳደሪያ ደንቡ ላይ አይቀመጥም” በማለት በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የተቀመጡት የበጎ አድራጎት ማኅበሩ “የማስመሰያ” ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.የቂም በቀል፣ ደም የመመለስ ወይም የጥቁር ደም፣ የነፍስ ግድያ ባህልና ግጭትን እንደ ጀግንነት የመቁጠር ልማድን ለኅብረተሰቡ በማስተማር ማስወገድ፣

2.ኋላ ቀር የሥራ ባህልን፣ ከአቅም በላይ መደገስንና አባካኝነትን፣ ያለ ዕድሜ ጋብቻን፣ የትዳር መፍረስንና የቤተሰብ መበተንን፣ ለዕድገትና ለሰላም ጠንቅ የሆኑ አስተሳሰብ አመለካከትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ኅብረተሰቡን በማስተማርና በማማከር ማስወገድ፣

3.በልዩ ልዩ ሱሶችና መጥፎ ልማዶች ተጠምደው ጎጂ ልማደኛ ሆነው ጎዳና ውስጥ ያሉ ወጣቶችን ካሉበት ሱስና መጥፎ ልማድ እንዲወጡ መርዳት፣

4.የአቅም ግንባታ የመልካም ሥራ ሠርቶ ማሳያ ልማቶችን መሥራት ናቸው፡፡

በማረሚያ ቤቶች ውስጥ በእርዳታ ሰበብ በመግባት በሃምሳ ስድስት (፶፮) ማረሚያ ቤቶች ላይ የእምነት ማስፋፋት ሥራ እየሠራች ሲሆን ታራሚዎቹ ሲወጡ በሚሔዱበት ቦታ የራሳቸው “ቸርች” እንዲያቋቁሙ ተልእኮ ትሰጣለች፡፡ በሃያ አንዱ (፳፩) ማረሚያ ቤቶች ደግሞ መደበኛ ሠራተኞች ተቀጥረው ይሠራሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ተቀጣሪዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዲቁናና በሰንበት ትምህርት ቤት ሲያገለግሉ የነበሩ ተሐድሶዎች ናቸው፡፡ ስውሩ የእምነት ማስፋፋት ሥራቸው እንዳይጋለጥ የተወሰኑ ማረሚያ ቤቶች ላይ የልማት ሥራዎችን ይሠራሉ፡፡ የተወሰኑ ማረሚያ ቤቶች ላይ ቤተ መጻሕፍትና ካፍቴሪያ ሠርተው ሰጥተዋል፡፡ ለታራሚዎች የልብስና የሳሙና እርዳታ ያደርጋሉ፡፡

መሠረተ ክርስቶስ ከእነዚህ ሁለት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች በተጨማሪ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በትምህርትና አቅም ግንባታ፣ በምግብ ዋስትና፣ በልማት፣ የተፈጥሮ አደጋን እና ኤች አይ ቪ ኤድስን በመከላከል ስም በመግባት ምእመናንን የመቀሰጥ ሥራ ትሠራለች፡፡ አዲስ አበባ፣ ናዝሬት፣ ደብረ ዘይት፣ ሆለታ፣ ማርቆስ፣ ሜታ ሮቢ፣ መሐል ሜዳ፣ ጀልዱ፣ ቀዋ ገርባ፣ ወዘተ እነዚህ ፕሮጀክቶች ተፈጻሚ የሆኑባቸውና ውጤት ያመጡባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ የልማት ሥራዎች መሠራታቸውን ማንም ኢትዮጵያዊ አይቃወምም፣ ነገር ግን በልማት ስም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናንን በመንጠቅ፣ ከማንነቱ መለየትና ከርስት መንግሥተ ሰማያት በኣፍአ እንዲቀር ማድረግ ተገቢ እንዳልሆነ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ እኛ የምንቃወመውም ርዳታውን እና ልማቱን ሳይሆን ከልማቱ በስተጀርባ ያለውንና ሰውን ከሃይማኖት መለየቱን ነው፡፡

የኢትዮጵያ አዲስ ኪዳን መጥምቃዊት ችርች ደግሞ በትምህርት ዘርፍ ላይ ተሰማርታ ሕፃናት ላይ ትኩረት አድርጋ የምትሠራ ናት፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች ትምህርት ቤት በመክፈት በቅናሽ ዋጋ እና ለወላጆች በሚደረግ ድጋፍ ስም የራሷን የእምነት ማስፋፋት ሥራ እየሠራች ነው፡፡ እስካሁን የእንቅስቃሴው አድማስ በሰሜን ሸዋ ዞን ዓለም ከተማ ወረዳ ላይ ቢሆንም ከተነደፈው ፕሮጀክትና ይዘውት ከተነሡት ግብ አንጻር በዚህ እንደማያቆም ግልጽ ነው፡

ሌላው መነሣት ያለበት ጉዳይ ባለፉት ቅርብ ዓመታት ትግራይ አካባቢ እየተካሔደ ያለው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ማኅበረ ሰላማ መወገዙ የሚፈልገውን የቅሰጣ ተግባር ከመሥራት አልከለከለውም፡፡ እንዲያውም አድማሱን አስፍቶ ከምእመናን ወጥቶ በየዩኒቨርሲቲው የሚማሩ ተማሪዎችን እና የቅዱስ ፍሬምናጦስ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርትን በመሰብሰብ በሥውር ማሠልጠንና ማስተማር ጀምሯል፡፡ ከማኅበረ ሰላማ በተጨማሪ ባለፈው ዓመት ትግራይ ተሐድሶ መንፈሳዊ ማኅበር (ቤተ ክርስቲያን) የሚባል የተሐድሶ ማኅበር ተመሥርቷል፡፡ ይህ ማኅበር ደንብ ቀርጾ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየን እየተካሔደ ያለው የተሐድሶ እንቅስቃሴ አድማሱ ምን ያህል ሰፊ እንደ ሆነና አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሰሜኑን የአገራችንን ክፍል ምን ያህል ትኩረት እንዳደረጉበት ነው፡፡

የአንድ አገር ልማትና ዕድገት ወደ ላቀ ደረጃ የሚደርሰው የሃይማኖት፣ የዘር፣ የቀለም ገደብ ሳይገድበው በተባበረ ክንድ ሲሠራ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው ሁሉ የአገሩን ልማትና የኅብረተሰቡን ዕድገት የሚጠላ አይሆንም፡፡ ሆኖም የልማቱ ተባባሪዎች ነን የሚሉ አካላት ፊት ለፊት ሰውን የሚያሳሱና መልካም የሚመስሉ ነገሮችን እያሳዩ ውስጣቸው ግን በማር የተለወሱ መርዞች ይዘውና ሌላ ተልእኮ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ከሆነ ልማቱም ልማት፣ ዕድገቱም የተሟላ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም አንድ ሕዝብ ለአገሩ ክብር፣ ለሃይማኖቱ ፍቅር፣ ለማኅበራዊ እሴቱ ዋጋ ከሌለው ማልማትም ማደግም አይችልምና፡፡

እስካሁን ያየናቸው በልማት ስም የተሠሩት ሥራዎች ደግሞ ውስጣቸው ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ ሴራ ያነገቡ የራስን አስተሳሰብና እምነት በሌ ሎች ላይ ለመጫን ዓላማ ያደረጉ ናቸው፡፡ ይህ ዓይነቱ አካሔድ ግን ፍትሐዊም ሃይማኖታዊም አይደለም፡፡ ልማትን እንደ መሸፈኛ ተጠቅመው የቀረቡት ከላይ የጠቀስናቸው ተግባራትም በቤተ ክርስቲያን ላይ የተነጣጠሩ የጥፋት ተልእኮዎች እንጂ አማናዊ ልማቶች ስላልሆኑ ዝም ተብለው መታየት የለባቸውም፡፡
ምንጭ፡- ስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጋዜጣ፣ 23ኛ ዓመት ቁጥር 3፣ ቅጽ 23 ቁጥር 331፣ ከጥቅምት 16-30 ቀን 2008 ዓ.ም

“ንቁ ቀርቶ ተናነቁ” ያሰኘው የምዕራብ ኢትዮጵያ የተሐድሶ እንቅስቃሴ

ኅዳር 14 ቀን 2008 ዓ.ም
ክፍል ዐራት
ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዕትሞች ስለ ተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ተከታታይ ጽሑፎችን ስናወጣ መቆየታችን ይታወቃል፡፡ ካለፈው ዕትም ጀምሮ ደግሞ የተሐድሶ መረብ አድማስና የትኩረት አቅጣጫን ማውጣት ጀምረናል፡፡ በዚህ መሠረት አዲስ አበባ እና ሰሜኑ የአገራችን ክፍል ላይ እየተካሔዱ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ለማሳየት ሞክረናል፡፡

የዚህ ጽሑፍ ቀጣይ የሆነውና በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ላይ እየተካሔደ ስላለው የተሐድሶ እንቅስቃሴ የሚዳስሰውን ሁለተኛ ክፍል ደግሞ እነሆ ብለናል፡፡ መልካም ንባብ፡-

የምዕራብ ኢትዮጵያ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ማእከላዊ ቦታ ምሥራቅና እና ምዕራብ ወለጋ ሆኖ ጅማ፣ ደንቢ ዶሎ፣ ሻምቡ፣ ከፋ፣ አሶሳና መቱን ያጠቃልላል፡፡ እንቅስቃሴው የሚመራው ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጆች ተመርቀናል በሚሉ ግለሰቦች ሲሆን በወረዳ ሊቃነ ካህንነት ደረጃ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችም አዲስ አበባ መጥተው የተለያዩ የተሐድሶ ሥልጠናዎችን ወስደው በመመለስ ለተሐድሶው አጋር የሆኑ ሰዎችን እያፈሩ ነው፡፡ በተለይም ቦንጋ፣ ምሥራቅ ወለጋና ምዕራብ ወለጋ ተሐድሶዎች ሰፊ መሠረት ለመጣል እየተንቃሳቀሱ ያሉባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ እንቅስቃሴው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላይ ባደረጉ ግለሰቦች ድጋፍ የሚመራና በቁሳቁስ፣ በገንዘብ፣ በአሳብና በሥልጠና እገዛ የሚደረግለት ነው፡፡

የእንቅስቃሴው መሪዎች የቤት ለቤት ቅሰጣ ከማድረግ አልፈው በአደባባይ የኑፋቄ ትምህርት ያስተምራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ምዕራብ ወለጋና ምሥራቅ ወለጋ ላይ በአጠቃላይ ዐሥር የእንቅስቃሴው መሪዎች ሥልጣነ ክህነታቸው ተይዞ ከማንኛውም አገልግሎት የታገዱ ሲሆን ቦንጋ ላይ ደግሞ አምስት ግለሰቦች የሚያስተምሩት ኑፋቄ በማስረጃ ተደግፎ ለሊቀ ጳጳሱ ቀርቦ ጉዳያቸው እየተጣራ ነው፡፡

ምዕራብ ወለጋ ላይ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሄኖክ ፊርማ ሥልጣነ ክህነታቸው ተይዞ ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የታገዱ የተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

.ሥዩም ስንታየሁ፡- የቄለም ወለጋ (ደምቢ ዶሎ) ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ማደራጃ ክፍል ሓላፊ የነበረ ሲሆን ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዲፕሎማ ተመርቋል፡፡ ሥዩም ስንታየሁ በቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት የተለያዩ ወረዳዎች ላይ በሚያስተምርበት ጊዜ፡-
ለአብርሃም የተገለጹለት ሁለት መላእክትና አንድ ሰው እንጂ ሥላሴ አይደሉም፣
€œእመቤታችን አታማልድም፤ የሚያማልደው በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤
ወትቀውም ንግሥት በየማንከ የሚለው ወይቀውም ንጉሥ በየማንከ፣ ወለገጽኪ ይተመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ የሚለው ወለገጽከ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ መባል አለበት፣
በኢሳይያስ ፷፣፲፬ እና በዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፪ ላይ ያለው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተነገረ አይደለም፣
ቅዱሳንን ማክበር አያስፈልግም፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እግራቸው የተቆረጠው በጦር ሜዳ ነው፣
ቅዱሳት ሥዕላት፣ ዝክር፣ ጽዋ፣ ተዝካር፣ አዋልድ መጻሕፍት አያስፈልጉም፣
ሥዕላት ለሕፃናትና ለደንቆሮዎች ማስተማሪያ እንጂ ለሌላ ለምንም አይጠቅሙም፣ ሥዕላትን መሳለምም ሆነ ማክበር አያስፈልግም፣
ከቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ሥር ያለው ሰይጣን ሳይሆን ማርቲን ሉተር ነው፣ ወዘተ የሚሉ የኑፋቄ ትምህርቶችን ማስተማሩ በማስረጃ ተረጋጋጦ ከግብር አበሮቹ ጋር ታኅሣሥ ፳፪ ቀን ፳፻ወ፯ ዓ.ም በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሔኖክ ፊርማ ታግዷል፡፡
ሥዩም ጅማ ሆሮ ወረዳ ላይ ለጉባዔ በሔደበት ወቅት የተወሰኑ ልጆችን ሰብስቦ ማታ ማታ ለብቻቸው የኑፋቄ ትምህርት ሲያስተምራቸው ነበር፡፡ ሲያስተምራቸው የነበሩትን ልጆች ሥዕለ ማርያምና ሥዕለ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እንዲቀዱ አድርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መድረክ በሚመራበት ጊዜ ጸሎት የሚያደርገው ዐይኑን ጨፍኖ ከመሆኑ በላይ አቡነ ዘበሰማያት ብሎ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል የማይደግምበትም ጊዜ አለ፡፡ ሥዩም ከቄለም ወለጋ ሲባረር ምሥራቅ ወለጋ ሔዶ መደበኛ ተቀጣሪ ሆኖ ለማገልገል ጥረት ቢያደርግም ከምሥራቅ ወለጋም ሊታገድ ችሏል፡፡

.እንዳለ ተፈሪ፡- የቄለም ወለጋ (ደምቢ ዶሎ) ሀገረ ስብከት ሰበካ ጉባዔ ማደራጃ ክፍል ሓላፊ የነበረ ሲሆን፡-
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አታስተምርም፣
እመቤታችን አታማልድም፤ የሚያማልደው በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤
ከአቡነ ዘበሰማያት ጋር በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መባል የለበትም፣
ድርሳናት፣ ገድላት እና ተአምረ ማርያም ደብተራዎች የደረሱዋቸው ስለሆነ አያስፈልጉም፡፡
ጽላት እና የኪዳን ጸሎት አያስፈልጉም፣
ቅዱሳን አያስፈልጉም በተለይም አቡነ ተክለ ሃይማኖት እግራቸው የተቆረጠው በጦር ሜዳ ነው፣
ለቅዱሳት መላእክት ክብረ በዓል ማድረግ አይገባም በሚሉት ኑፋቄዎቹ ከማንኛውም አገልግሎት እንዲታገድና ሥልጣነ ክህነቱ እንዲያዝ ተደርጓል፡፡

.ገመቺስ ዘሪሁን፡- የዳሌ ሰዲ ወረዳ ቤተ ክህነት ሰባኬ ወንጌል ክፍል ሓላፊ ሲሆን፡-
እመቤታችን አታማልድም፤ የሚያማልደው በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤
ገድላት፣ ድርሳናትና መዝገበ ጸሎት ከቤተ ክርስቲያን መውጣት አለባቸው፣
ጽዋ፣ ዝክር፣ ተዝካር፣ አዋልድ መጻሕፍት አያስፈልጉም፣
ቅዱስ ሲኖዶስ በ፳፻ወ፬ ዓ.ም የገናና የሐዋርያት ጾም አምስት፣ አምስት ቀናት ብቻ ይበቃል ብሎ ወስኗል በማለት የራሱን የሐሰት ትምህርት ቤተ ክርስቲያን የደገፈችው ለማስመሰል ከመጣሩም በላይ፣
ዳሌ ወረዳ ዓለም ተፈሪ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተወሰኑ ልጆችን ሰብስቦ የተሐድሶ መናፍቃንን መጽሐፍ ሲያድል በመገኘቱ፣
ጾም አያስፈልግም ብሎ በማስተማሩ እና እሱም ረቡዕ እና ዐርብ እንደሚበላ በመረጋገጡ በሀገረ ስብከቱ ከማንኛውም አገልግሎት እንዲታገድና ሥልጣነ ክህነቱም እንዲያዝ ተወስኖበታል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ተሐድሶዎች በየቦታው ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ፣ ምእመናንን ከርትዕት ሃይማኖት ለመነጠል ምን ያህል እየሠሩ መሆኑን ነው፡፡ የሚያስተምሩት ትምህርትም የለየለትን ግልጽ የፕሮቴስታንት ምህርት መሆኑ ከላይ ካየናቸው ትምህርቶቻቸው መረዳት ይቻላል፡፡

ከእነዚህ ግለሰቦች በተጨማሪ ሀገረ ስብከቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው ስውር የተሐድሶ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ መሆናቸው ማስረጃ የቀረበባቸውን ግለሰቦች በስም ጠቅሶ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ደብዳቤ ጽፏል፡፡ ግለሰቦቹ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በግ መስለው ገብተው በሚያስተምሩት ትምህርት ተኩላነታቸው በፍሬያቸው የተገለጸባቸውና በማስረጃ ተደግፎ የቀረበባቸው ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው ቤተ ክርስቲያንን እየተዋጓት ያሉትየውስጥ አርበኞች ደግሞ በደብዳቤው ላይ በተጠቀሰው መሠረት የሚከተሉትን ኑፋቄዎች የሚያሠራጩ ናቸው፡፡ በአቤቱታው ላይ በስም ቢጠቀሱም በሀገረ ስብከቱ ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጉዳያቸው ተመርምሮ ውሳኔ እስከሚሰጣቸው ድረስ ስማቸውን መጥቀስ አስፈላጊ መስሎ ስላልታየን አልፈነዋል፡፡

፩ኛ ተጠርጣሪ፡- የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበረ ሲሆን አቤቱታ የቀረበበትም፡-
የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሳለ በሓላፊነቱ ከቤተ ክርስቲያን አበል እያወጣ ኦርቶዶክሳዊ ሥልጠና አስመስሎ የተሐድሶ ሥልጠና ሲያዘጋጅ ነበር፣
የክርስቶስ አምላክነት በቤተ ክርስቲያን እየተሰበከ አይደለም፣
የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ትክክል አይደለም፣
ታቦትና ንስሐ አባት አያስፈልጉም፣ እነዚህ እስኪቀሩ ድረስ እታገላለሁ፣ በማለቱ ምክንያት ነው፡፡

፪ኛ.ተጠርጣሪ፡-መቀመጫውን አዲስ አበባ አድርጎ ከቤተ ክርስቲያኗ መዋቅር ውጪ የሰባክያን ማኅበር የሚባል ቡድን በማደራጀት እሰብካለሁና እዘምራለሁ በሚል ሰበብ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ብዙ ጥፋቶችን ያደረሰ ነው፡፡ እመቤታችን፣ ቅዱሳን መላእክትና ጻድቃን አያማልዱም፣ ልክ እንደ ማይክራፎን መልእክት ማስተላለፍ ብቻ ነው፡፡ የሚል የኑፋቄ ትምህርት ማስተማሩ በማስረጃ ተደግፎ ቀርቦበታል፡፡

፫ኛ.ተጥጣሪ፡-በ፳፻ወ፬ ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የተወገዘው ማኅበረ ሰላማ የሚባለው የተሐድሶ ድርጅት አባል ሲሆን በኪልጡ ካራ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አብነት ትምህርት ቤት ሁለተኛ ዐመት ተማሪ ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ሳለ፡-
ውዳሴ ማርያም፣ መልክአ መልክእ፣ ሰዓታትና ማኅሌት አያስፈልጉም፣
አዋልድ መጻሕፍት ማለትም ገድላት፣ ድርሳናት አያስፈልጉም፣
በቅዱሳን አማላጅነት መታመንና መታሰቢያ ማድረግ አስፈላጊ አይደለም፣
ሥጋ ወደሙ መፈተት የነበረበት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንጂ ጽላት ላይ መሆን አልነበረበትም፣
ቤተ ክርስቲያን የሰውን ታሪክ በማስተማር ዝባዝንኬ ታበዛለች፣ ማለቱ አብረውት በሚማሩት ተማሪዎች የተረጋገጠበት ነው፡፡

ደብዳቤው አይይዞም ዮሐንስ ጌታሁን የሚባል ከቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መንፈሳዊ የትምህርት ተቋም የተመረቀ ሲሆን በአሁን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ፕሮቴስታንት ሆኖ ብዙ ሰዎችን እያሳተ እንደሚገኝ ይጠቅሳል፡፡ በተጨማሪም ጽጌ ሥጦታውን እንዲያስተምር የሚጋብዙት፣ የአግዛቸው ተፈራን መጽሐፎች የሚያከፋፍሉት ከከፍተኛ መንፈሳዊ የትምህርት ተቋማት ተመረቅን የሚሉ ጾም አያስፈልግም በማለት ጠዋት ተነሥተው በሚያስተምሩት ምእመን ፊት የሚበሉ አገልጋይ ነን ባዮች እንደሆኑ ይገልጻል፡፡ መድረክ ላይ ቆመው የሚያስተምሩት ደግሞአርዮስ ምሁር ነው አልተወገዘም፣ ተወግዟል የሚሉት አላዋቂዎች ናቸው በማለት አርዮስን የሚያሞጋግሱ እንደሆኑ በደብዳቤው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ላይ የተሐድሶ እንቅስቃሴው ፊት አውራሪ ሆነው ሀገረ ስብከቱን ሲፈትኑት የነበሩትን ሰዎች ሀገረ ስብከቱ ሥልጣነ ክህነታቸው ተይዞ ከአገልግሎት እንዲታገዱ አድርጓል፡፡ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ስምዖን ፊርማ ሥልጣነ ክህነታቸው ተይዞ ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የታገዱት የምሥራቅ ወለጋ የተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪዎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡

፩. ሳሙኤል ታከለ- የሞጤ/ዋማ ወረዳ ቤተ ክህነት ሓላፊ የነበሩ ሲሆን ሥልጣነ ክህነታቸው የተያዘ እና ከማንኛውም አገልግሎት የታገዱ ናቸው፣
፪.ዲ/ን€ ቶላ በየነ፡- በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ስሬ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበረው ዲ/ን ቶላ በየነ ከዚህ በፊትም የኑፋቄ ትምህርት በማስተማሩ ምክንያት ከማንኛውም ዐይነት የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በወረዳ ቤተ ክህነቱ ታግዶ ቆይቷል፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ የታገደው ግለሰብ የኑፋቄ ትምህርት ማስተማሩን ሳይተውና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚያዘውን ሳይፈጽም (ተጸጽቶ ንስሐ ሳይገባና ተምሮ ሳይስተካከል) የካቲት ፩ ቀን ፳፻ወ፯ ዓ.ም በስሬ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን በሥርዓተ ተክሊል ጋብቻውን ሊፈጸም ችሏል፡፡ ቶላ በየነ ምዕራብ ወለጋ ላይ እንደሚገኙት ጓደኞቹ የተወሰኑ ወጣቶችን ሰብስቦ €œየሐዲስ ኪዳን ልጆች€ በሚል ለብቻቸው የኑፋቄ ትምህርት እንደሚያስተምርም ተደርሶበታል፡፡ በዚህም ምክንያት ሀገረ ስብከቱ ከማንኛውም አገልግሎት አግዶ ሥልጣነ ክህነቱ እንዲያዝ አድርጓል፡፡
፫.€ቄስ€ ሙሴ ዘሪሁን፡- ሥልጣነ ክህነቱ የተያዘ እና ከማንኛውም አገልግሎት የታገደ፣
፬.€œዲ/ን€ ነቢዩ ጀምበሬ፡- ከሥልጣነ ክህነቱ ሙሉ በሙሉ የተሻረ እና ከማንኛውም አገልግሎት የታገደ፣
፭.€œዲ/ን€ ዓለማየሁ አየልኝ፡- ሥልጣነ ክህነቱ የተያዘ እና ከማንኛውም አገልግሎት የታገደ፣
፮.€œዲ/ን€ ታረቀኝ ፈቃዱ፡- ሥልጣነ ክህነቱ የተያዘ እና ከማንኛውም አገልግሎት የታገደ፣
፯.ወጣት ኢታና ዲንቂሳ፡- ከማንኛውም አገልግሎት የታገደ ናቸው፡፡

ሀገረ ስብከቱ ከምእመናን በቀረበለት ጥቆማ መሠረት እነዚህ ግለሰቦች ሲያደርጉት የነበረውን የምንፍቅና እንቅስቃሴ ሲከታተል ከቆየ በኋላ የቀረበው ጥቆማ እውነት መሆኑን በማረጋገጡ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ስምዖን ፊርማ ከማንኛውም አገልግሎት እንዲታገዱና ሥልጣነ ክህነነታቸው እንዲያዝ ወስኗል፡፡ ከእነዚህ ሰባት ግለሰቦች በተጨማሪ ምዕራብ ወለጋ ላይ የታገደው ሥዩም ስንታየሁ ምሥራቅ ወለጋ አንዳንድ አካባቢዎች በመግባት ለማስተማር ይንቀሳቀስ ስለ ነበር በክፍሉ ሊቀ ጳጳስ መታገዱን የተረዳው የምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ከማንኛውም አገልግሎት አግዶታል፡፡ ተሐድሶ መናፍቃን ኑፋቄያቸው ሲገለጽባቸው ተጸጽተው ንስሐ እንደ መግባትና ተምረው እንደመስተካከል በአንድ አካባቢ ሲነቃባቸው ማንነታቸውን ደብቀው በሌላ አካባቢ እንደሚንቀሳቀሱ ይህ ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡

ሀገረ ስብከቱ ከላይ ከተጠቀሱት ግለሰቦች በተጨማሪ መሠረተ ክርስቶስ ቸርች ባዘጋጀችው ሥልጠና ላይ ተገኝተው ውስጥ ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ ተልእኮ ተሰጥቷቸው የሔዱ ሦስት የወረዳ ሊቃነ ካህናት ላይ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች መሠረተ ክርስቶስ ቸርች ከግንቦት ፳፭ እስከ ሰኔ ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ድረስ ደብረ ዘይት መሠረተ ክርስቶስ ኮሌጅ ለዐሥር ቀናት ያህል ሲሰጥ በነበረው ሥልጠና ላይ ተሳታፊ የነበሩ እና አበል በስማቸው ፈርመው የተቀበሉ ናቸው፡፡ ከሥልጠናው በኋላ ሌሎችን የወረዳ ቤተ ክህነት ሊቃነ ካህናትን ለተሐድሶ እንዲያዘጋጁ ሓላፊነት የተሰጣቸው ናቸው፡፡ ሦስቱም በአንድነት ከተመደቡበት ወረዳ የተለያዩ ምክንያቶችን እያቀረቡ ይወጣሉ፡፡

ሌላው የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ያየለበት ቦታ ቦንጋና አካባቢው ሲሆን የዚህን አካባቢ እንቅስቃሴ የሚመሩት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጆች የተመረቁ ግለሰቦች ናቸው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ከኮሌጅ ከተመረቁበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ትክክል አይደለም የሚል ትምህርት በስውር ያስተምሩ ነበር፡፡

የቦንጋና አካባቢው የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ እንደ ሌሎቹ አካባቢዎች በስውር የሚካሔድ ሳይሆን ተሐድሶዎቹ ቤተ መቅደስ ድረስ ገብተው አዲስ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የሚፈጥሩበት ዐይን ያወጣ የክህደት እንቅስቃሴ የሚካሔድበት ነው፡፡
ካህናቱ በሚቀድሱበት ጊዜ ቅድስተ ቅዱሳኑ በመጋረጃ መሸፈን የለበትም፣ ካህናቱን የምትሠሩትን ሁሉ መመልከት አለብን ብለው የቅድስተ ቅዱሳኑ መጋረጃ ተከፍቶ እንዲቀደስ እስከ ማድረግ ደርሰዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ዶግማ መፋለስ፣ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መጣስ፣ የምእመናንን እንግዳ በሆነ አዳዲስ ትምህርት ግራ መጋባትና ከቤተ ክርስቲያን መፍለስ እና የአካባቢው በመናፍቃን መወረስ ያሳሰባቸው ካህናትና ወጣቶች እነዚህን ግለሰቦች ሲከታተሉ ቆይተው ያስተማሩትን የኑፋቄ ትምህርት በማስረጃ አስደግፈው ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል አቅርበዋል፡፡ ከካህናትና ከምእመናን ለብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል አቤቱታ የቀረበባቸው የቦንጋ እና አካባቢው ተሐድሶ አንቀሳቃሾች የሚከተሉት ናቸው፡፡
፩ኛ.ተጠርጣሪ፡-በ፲፱፻፺፯ ዓ.ም የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ እያለ የኮሌጁን ደንብ የጣሰ ተግባር በመፈጸሙ ክስ ተመሥርቶበት ተባርሮ የነበረና ከአምስት ዓመታት በኋላ በ፳፻ወ፪ ዓ.ም ለመንፈሳዊ ኮሌጁ ጥፋቱን በማመን የይቅርታ ደብዳቤ አስገብቶ ወደ ኮሌጁ የተመለሰ ነው፡፡ ወደ ኮሌጁ በተመለሰበት ወቅት በከፋ ሀገረ ስብከት በተለይም በቦንጋ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ የእርሱን ደጋፊዎች በማሰባሰብ ተቀባይነት ለማግኘት በሠራው ሥራ የብዙዎችን ልብ መግዛት ችሎ ነበር፡፡

በቤተ ክርስቲያን በበጎ አገልግሎታቸው የሚታወቁትን አገልጋዮች ስም በማጥፋት፣ በዘርና በፖለቲካ በመከፋፈል በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ላይ ሳይቀር ሕዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ በማድረግ ቤተ ክርስቲያንን ሲያምስ ነበር፡፡ በዚህ ድርጊቱ ብዙዎቹ ከቤተ ክርስቲያን ሲቀሩ፣ የተወሰኑት ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ጥለው ወጥተዋል፡፡

አዲስ አበባ ተቀምጦ ብዙዎችን አጥቢያዎች እስከ ማዘዝ የሚደርስ ሥልጣን ያለው ነበር፡፡ በራሱ ፈቃድ ሰባኪና ዘማሪ እየመረጠ በመላክ ጉባዔ የሚያዘጋጀው፣ ለወንጌል አገልግሎት በሚል ከተለያዩ አካላት ገንዘብ የሚሰበስበው፣ አጥቢያዎች በማያውቁበት ሁኔታ የባንክ አካውንት የሚከፍተው፣ ወጣቶችን በማሰባሰብና ልዩ ሥልጠናዎችን የሚሰጠውና አዲስ አበባ በማስመጣት በተለያዩ የመናፍቃን አዳራሾች ሥልጠና እንዲወስዱ የሚያደርገው እርሱ ነበር፡፡

በእርሱ አመራር የሠለጠኑት ወጣቶች በግልጽ ታቦት አያስፈልግም፣ እኛ ከቅዱሳን እኩል ነን፣ እኔ ከድንግል ማርያም ጋር እኩል ነኝ፣ የቤተ መቅደሱን አገልግሎት በማናናቅ በእነርሱ ቋንቋተረት ተረት አያስፈልግም ክርስቶስ ብቻ ይሰበክ የሚሉ የክህደት ትምህርቶችን የሚያስተምሩ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በድፍረት የሚጥሱ፣ ካህናትን እና ዲያቆናትን የሚሳደቡ ሆነዋል፡፡ የተሐድሶ አቀንቃኝ ሰባኪዎችን በማስተባበር ወደ ቦንጋ በመውሰድ ክርስቶስ አልተሰበከምክርስቶስን ብቻ ስበኩ፣ ወዘተ እያለ ሕዝቡን ግራ ያጋባ ነበር፡፡ በደብረ ዘይት ዕለት ለጉባዔው ድምቀት ከበሮ ቢመታ ችግር የለውም በሚል የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ወደ ጎን በመተው ከበሮ እንዲመታ ሲያደርግ ካህናቱ ትክክል እንዳልሆነ ሲነግሩት ሊሰማቸው አልቻለም፡፡

ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተብሎ የተገዛውን ሞንታርቦ ለዋዜማና በንግሥ ወቅት ታቦት ቆሞ ለማስተማር ሲጠየቅ ሞንታርቦው የተገዛው ለወንጌል እንጂ ለተረት ተረት አይደለም በማለት በድፍረት ይናገራል፡፡ እርሱ በሚመራቸው ወጣቶች ለአገልግሎት በተሰጣቸው መቃብር ቤት ውስጥ ዘጠኝ የመናፍቃን ማሠልጠኛ መጻሕፍት መገኘታቸውና ልጆቹም ማመናቸው በደብዳቤው ተጠቅሷል፡፡

፪ኛ.ተጠርጣሪ፡-በቦንጋ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ የነበረ ሲሆን ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቀ ነው፡፡ በኮሌጅ ቆይታው ከተለያዩ የተሐድሶ መናፍቃን ድርጅቶች አስተባባሪዎች ጋር ይገናኝ ነበር፡፡ የኮሌጁን ተማሪዎችም ከእነዚህ የተሐድሶ ድርጅቶች ጋር የማገናኘት ሥራ ይሠራ ነበር፡፡ ክረምት እና እረፍት ወቅት ወደ ቤተሰቦቹ ሲሔድ የተወሰኑ የአጥቢያው ዲያቆናትንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን በመሰብሰብ ቅዱሳን አያማልዱም፣ አዋልድ መጻሕፍት አያስፈልጉም፣ መቅደስ ውስጥ ክህነት ያለው ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ሰው መግባት ይችላል፣ ክብር ይግባትና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት እያለ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ያልሆነ ኑፋቄ ያስተምራል፡፡

ከተመረቀም በኋላ ወደ ተመደበበት ሀገረ ስብከት ሳይሔድ ጀምሮት የነበረውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ አዲስ አበባ ላይ ተቀምጦ መምራት ጀመረ፡፡ አዲስ አበባ ላይ የሚታወቅ ቋሚ ገቢ ሳይኖረው ኮንዶሚንየም ቤት ተከራይቶ የኮሌጁን ተማሪዎች በማስተባበር ወደ ቤቱ እየወሰደ የቅሰጣ ተግባሩን ቀጠለበት፡፡ እንቅስቃሴው በአዲስ አበባ ብቻ ሳይገታ ከወንድሙ ጋር በመሆን ቦንጋ ላይ ዘወትር እሑድ ጠዋት ኮርስ በሚል ሰበብ ልዩ የተሐድሶ ሥልጠና በማዘጋጀት ብዙ ወጣቶችን ያስተምር ነበር፡፡ በዱባይ ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚያስተምሩት መምህራን አንዱ ነው፡፡

ኛ.ተጠርጣሪ፡-ነዋሪነቱ ቦንጋ አካባቢ ሲሆን በ፲፱፻፺፯ ዓ.ም በግብርና ባለሙያነት ከቴክኒክና ሙያ በዲፕሎማ ተመርቆ ጨና ወረዳ ላይ ለአንድ ዓመት ያህል ከሠራ በኋላ ሥራውን ለቆ ወደ ቦንጋ መጣ፡፡ በ፳፻ ዓ.ም ዲቁና የተቀበለው ሲሆን በ፳፻ወ፫ ዓ.ም መንፈሳዊ ኮሌጅ ለመግባት ጠይቆ ኮሌጅ ገብቶ ለመማር የሚያበቃው መነሻ የሚሆን የቀደመ ትምህርት የለውም የሚል አቤቱታ በምእመናኑ ስለቀረበበት ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

የቦንጋ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ካህናት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ የእመቤታችንን ክብር በማቃለልና ለሌሎችም በማስተማር፣ ሥርዓት ቤተ ክርስቲያን በመጣስና ካህናትን ከቤተ ክርስቲያን ለማሳደድ ወጣቱን እያደራጀሁ ነው ብሎ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ መዘጋጀቱን በመናገሩ ዐጽራረ ቤተ ክርስቲያን መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

፬ኛ.ተጠርጣሪ፡-ክርስቶስ አማላጅ ነው፤ ታቦት አያስፈልግም፣ ወዘተ የሚሉ ኑፋቄዎችን የሚያስተምር እንደሆነ አቤቱታ ቀርቦበታል፡፡

፭ኛ.ተጠርጣሪ፡-ክርስቶስ አሁንም አማላጅ ነው፤ ማርያም ሕጸጽ አለባት፤ ማኅሌት ከሚቆም ኢየሱስ ቢሰበክ ይሻላል፤ ተአምረ ማርያምም ሆነ ሌሎች አዋልድ መጻሕፍት አያስፈልጉም፤ ጸሎታ ለማርያም የሚለው ጸሎት አይስፈልግም፤ ታቦት አያስፈልግም፤ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ትችላለች€ በሚሉ ኑፋቄዎቹና በእጁ ዘጠኝ የተሐድሶ ማሠልጠኛ መጻሕፍት በመገኘታቸው በማኅበረ ካህናቱ አቤቱታ የቀረበበት ነው፡፡

በአጠቃላይ እነዚህ ግለሰቦች ውዳሴ ማርያም ሲደገም ጸሎት ረግጠው የሚወጡ፣ ካህናት የያዙትን መስቀል በማጣጣል መስቀል አንሳለምም የሚሉ ልጆችን በአምሳላቸው ቀርፀው ያወጡ፣ ክርስቶስ በቤተ ክርስቲያን አልተሰበከም የሚሉ፣ የካህናት ዐይናቸው አልበራም ብለው አባቶችን የሚሳደቡ፣ ካህናት ሲናዝዙ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ብቻ እንጂ በእንተ እግዝእትነ ማርያም ማለት ትክክል አይደለም ብለው የሚቃወሙ መሆናቸው በከፋ ሀገረ ስብከት የቦንጋ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ካህናት አቤቱታ የቀረበባቸው ናቸው፡፡ ሀገረ ስብከቱም ከማኅበረ ካህናቱ የቀረቡትን አቤቱታዎች በመመርመር ላይ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ያለ ደብሩ ዕውቅና ምንም ዐይነት ጉባዔ እንዳይካሔድ በተለይም በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የሌሉ ሰዎች ጉባዔያት እንዳያካሒዱ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በደብዳቤ አግደዋል፡፡

የምዕራቡ የአገራችን ክፍል የተሐድሶ እንቅስቃሴ እንዳየነው ጠንከር ያለ እና ሥር የሰደደ ነው፡፡ በዚያው ልክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅና ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ አደራ ያለባቸው ኦርቶዶክሳውያንም ከተሐድሶዎች ጋር የሚያደርጉት ትንቅንቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው፡፡ በተለይም የምሥራቅ ወለጋ እና የምዕራብ ወለጋ አኅጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ተሐድሶዎችን በመለየት ከአገልግሎት ማገዳቸውና ሥልጣነ ክህነታቸውን መያዛቸው ለምእመኑ እፎይታ የሰጠ፤ ለሌሎችም አኅጉረ ስብከት አርአያ የሚሆን ተግባር ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አሐቲ፣ ኩላዊትና ሐዋርያዊት የሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን!!!

ምንጭ፡- ስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጋዜጣ፣ 23ና ዓመት ቁጥር 1/ቅጽ 23፣ ቁጥር 333፣ ኅዳር 1-15 ቀን 2008 ዓ.ም

መንፈሳዊ ኮሌጆችና “ደቀ መዛሙርቱ” ምን እና ምን ናቸው?

ኅዳር 21 ቀን 2008 ዓ.ም
ክፍል አምስት
የተሐድሶ መረብ አድማስና የትኩረት አቅጣጫዎች በሚል ባለፉት ሁለት ዕትሞች ስለ አዲስ አበባ፣ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ፣ ስለ ምዕራብና ደቡብ ኢትዮጵያ የተሐድሶ መናፍቃን አቅርበንላችሁ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ መንፈሳዊ ኮሌጆችን መሠረት ያደረገውን የተሐድሶ መናፍቃንን ዒላማ ከብዙው በጥቂቱ፣ ከረጅሙ በአጭሩ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡

ተሐድሶ መናፍቃን ቤተ ክርስቲያንን ፕሮቴስታንት የማድረግ ዕቅዳቸውን ዕውን ለማድረግ ትኩረት ካደረጉባቸው ተቋማት መካከል የመጀመሪያዎቹና ግንባር ቀደሞቹ የመንፈሳዊ ኮሌጆችደቀ መዛሙርት€ ናቸው፡፡ እስካሁን በማኅበር ደረጃ የሚንቀሳቀሱት ከሃያ አምስት በላይ የተሐድሶ መናፍቃን ድርጅቶች ቀላል የማይባሉ አባሎቻቸው በመንፈሳዊ ኮሌጆች ተምረው ያለፉ፣ ይሠሩ የነበሩ ወይም በመሥራት ላይ የሚገኙ እንዲሁም የሚማሩ ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ የሚታየው የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ከተማሪዎች ምልመላ እና ተማሪዎቹ ወደ ኮሌጆቹ ሲገቡ ከሚደረግላቸው ቅበላ ጀምሮ የሚሠራ ነው፡፡ የገንዘብ እጥረት የሚያጋጥማቸውን ደቀ መዛሙርት ደግሞ በድጋፍ ስም ይቀርቧቸዋል፡፡ መጻሕፍትንና ሌሎች አስፈላጊ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን በመዋዋስ ስም ግንኙነት በመፍጠር ኦርቶዶክሳዊ ተማሪዎችን ወደ ቡድናቸው ያስገባሉ፡፡

ከተለያዩ መንፈሳዊ ኮሌጆች የተመረቁ €œደቀ መዛሙርት€ ኅቡዕ ቡድን መሥርተው በቤተ ክርስቲያን ላይ ሰፋ ያለ ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ቡድኑ ዓላማውን ለማሳካት በተለያዩ ቦታዎች ላይ ተወካይ በማስቀመጥ ሥራውን ይሠራል። ይህ ስውር ቡድን በመጨረሻ ላይ ለማሣካት ዓላማ አድርጌ ተነሣኋቸው የሚላቸው የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በራሳቸው መንገድና የኑፋቄ አቅጣጫ በመለወጥ ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ ካስቀመጣቸው የማስመሰያ ግቦች፡-
ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቃል በምልዓት እንዲኖርባቸው ማድረግ፣
በሥነ መለኮት ትምህርት ገንቢ ዕውቀት ያላቸውን አገልጋዮች በማደራጀት የወንጌልን እን ቅስቃሴ ማስፋፋት፣
 በቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ ከስንዴ ጋር አብረው የገቡትን ትምህርቶችና መጻሕፍት (አስተምህሮዎች) ማስወገድ፣
 ቤተ ክርስቲያን ምንም ከማይጠቅም ወግ፣ ልማድ እና በብልሃት ከተፈጠሩ ተረታዊ ትምህርቶች ተለይታ እውነት የሆነው ክርስቶስ እንዲሰበክ ማድረግ፣
 የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት በክርስቶስ ጥላ ሥር ተሰብስበው እንዲያመልኩና በአንድ እንዲተባበሩ ማድረግ፣
 ወንጌል በእያንዳንዱ ቤት አንኳኩቶ በመግባት መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ፣
 ወጥና ተከታታይ ትምህርትን በማዘጋጀት ወጣቶችን፣ ሕፃናትንና አረጋውያንን በማነቃቃት ለዓለም ብርሃን የሆነውን የጌታን ቃል ለሁሉም እንደየአቅማቸውና እንደየደረጃቸው ማዳረስ፣
 በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት መሥራት፣
 የወንጌልን ተልእኮና ለውጥ ሊያፋጥን በሚቻል መልኩ የተለያዩ ተቋማትን ማእከል በማድረግ መንቀሳቀስ፣
 የቤተ ክርስቲያን ለውጥና ዕድገት የሚሹትን ሁሉ ማደራጀት፣
 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እራሱን የቻለ ማኅበር ማቋቋም የሚሉ ናቸው፡፡ (ምንጭ፡- የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ገጽ ፺፬)

እነዚህን እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች በመደርደር €œቤተ ክርስቲያናችን እስካሁን ድረስ ዘመናትን የፈጀችው ወንጌልን ስትሰብክ ሳይሆን ስለ ቅዱሳን ስታስተምር ነው፤ አሁን መስበክ ያለብን ክርስቶስን ነው€ የሚለውን ተሐድሶ መናፍቃን ያራምዱት የነበረውን የፕሮቴስታንት አስተምሮ ይዞ የተነሣ ነው። ለቅዱሳን የማስተማር ጸጋ ስለሰጣቸው ስለ ክርስቶስ ማስተማር መሆኑን መረዳት ይገባቸዋል ቤተ ክርስቲያን ጉልላቷ ስለሆነው ስለ ክርስቶስ ሳታስተምር የዋለችበት ዕለት ያለ ለማስመሰል መሞከራቸው ስሕተት ነው፡፡ ዓላማዬን ያሳኩልኛል ብሎ ካሰማራቸው ሰዎች ሲገልጽ ደግሞ እንዲህ ብሏል፡፡ ሥራውን የሚሠራው መንፈስ ቅዱስ ሆኖ የለውጥ መሪ የሚሆኑ በእምነትና በዕውቀት የታመነባቸው የነገረ መለኮት ተማሪዎች፣ ልዩ ልዩ መምህራን፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግሉ ቀሳውስትና ዲያቆናት፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ምእመናን፣ ልዩ ልዩ ድርጅቶች ናቸው፡፡ ይህ ሲባል በመንፈሳዊ ለውጥ የሚሠሩትን አካላትም ያካትታል፡፡

ቡድኑ በዋነኝነት በመንፈሳዊ ተቋማት ያሉና ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎችን ቢያማክልም በግላቸውና በማኅበር ተጀራጅተው ከሚንቀሳቀሱ ማኅበራት ጋር አብሮ ይሠራል። ይህ ማኅበር ዓላማውን ለማሳካት የምንፍቅናውን መርዝ ለመርጨት ያሰበባቸው ቦታዎች መንፈሳዊ ኮሌጆች ብቻ ሳይሆኑ፤ የካህናት ማሠልጠኛ ሥፍራዎች፣ ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ የቤተ ክህነት መሥሪያ ቤቶች፣ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት እና ማኅበራት ናቸው፡፡
ለእንቅስቃሴው አስተዋጽኦ ያደረጉ ሁኔታዎች
በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ ያለው የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታዩ ከኮሌጆቹ አስተዳደራዊ መዋቅርና አሠራር እንዲሁም ከተማሪዎች ክትትል ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

፩.አስተዳደራዊ ችግሮች
መንፈሳዊ ኮሌጆች ላይ የሚከሠቱት የአብዛኛዎቹ ችግሮች መነሻቸው አስተዳደራዊ ችግር ነው፡፡ ይህ የሁሉም ችግሮች ምንጭ ነው፡፡ መንፈሳዊ ኮሌጆች አስቀድመው አስተዳደራዊውን ችግር ቢፈቱ ሌሎችን በቀላሉ መፍታት ይችላሉ፡፡ ከገንዘብ አያያዝ፣ ከተማሪዎች ጋር ባለው መልካም ግንኙነት፣ ከመምህራን ቅጥር እና ከአስተዳደር ሓላፊዎች ምደባ ጋር ተያይዞ ብዙ ችግሮች ይታያሉ፡፡ እነዚህ አስተዳደራዊ ችግሮች ተቋሙ ዋና ጉዳዩ የሆኑት ደቀ መዛሙርትን ዘንግቶ ሌሎች ጉዳዮች ላይ እንዲጠመድ ያደርጉታል፡፡ ተሐድሶ መናፍቃኑ ደግሞ ይህንን ክፍተት በደንብ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ አስተዳደራዊውን ችግር ሃይማኖታዊ አስመስሎ ከማቅረብ ጀምሮ በየጊዜው ለአስተዳደሩ የቤት ሥራ የሆኑ ጉዳዮችን በመብት ስም እያነሡ እነርሱ የውስጥ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ይተጋሉ፡፡
፪.የገንዘብ እጥረትና የአጠቃቀም ችግር
ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንደ አንድ ችግር የሚነሣው የገንዘብ እጥረት ነው፡፡ በእርግጥ ቤተ ክርስቲያን ከማንኛውም አካል በላይ የሆነ ሀብት አላት፡፡ ይህም ሀብት የልጆቿ ዕውቀት፣ ጉልበትና ገንዘብ ነው፡፡ ይህንን በአግባቡ አቀናጅቶ የሚያሠራ መዋቅር፣ አሠራርና ስልት ባለመዘርጋቱ ግን ብዙ አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚሰጥባቸው ጠፍቶ ሲዘጉ ይታያሉ፡፡ ከተማ ላይ አብያተ ክርስቲያናት በሚልዮንና ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሲያንቀሳቅሱ፣ እያንዳንዳቸው ከአንድ መቶ በላይ አገልጋዮች ሲኖሯቸው በገጠር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ በአንጻሩ ዕጣንና ጧፍ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን የሚከፍት አንድ ካህን አጥተው ሲቸገሩ ይታያል፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማእከላዊ የሆነ የገንዘብ አያያዝ ባለመኖሩ የተከሠተ ችግር ነው፡፡
የዚህ ችግር ውጤትም በአጥቢያዎች ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ በሚገኙ ተቋማትም የሚታይ ነው፡፡ መንፈሳዊ ኮሌጆች በዚህ ከሚፈተኑት የቤተ ክርስቲያን ተቋማት መካከል ናቸው፡፡ ኮሌጆቹ እንደ ተቋም ለአገልግሎቱ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ለማሟላት የገንዘብ እጥረት ያጋጥማቸዋል፡፡ ይህ ክፍተት ደግሞ በእርዳታ ስም መናፍቃኑ ወደ ተቋማቱ እንዲገቡ በር ከፈተላቸው፡፡ በመንፈሳዊ ኮሌጆች የሚማሩ ደቀ መዛሙርትም ወደ ሌላ እምነት እንዲገቡና የተሐድሶ መናፍቃኑን ጎራ እነዲቀላቀሉ ከሚያደርጓቸው ችግሮች አንዱ የገንዘብ እጥረት ነው፡፡

፫.የምልመላ መስፈርት
ተማሪዎች ወደ ኮሌጆች የሚገቡት ከዚህ በፊት የነበራቸው ሰብእና (ማንነትና ምንነት) ተጠንቶና ታውቆ ሳይሆን ሀገረ ስብከት ላይ ወደ መንፈሳዊ ኮሌጆች ለመላክ ሓላፊነት ካላቸው አካላት ጋር ባላቸው ቅርበት ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ብዙ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ፣ ትልቅ አቅም ያላቸው ሰዎች እየቀሩ በጓደኝነት፣ በዝምድና፣ አለፍ ሲልም በጥቅማ ጥቅም ወደ ኮሌጆች የሚገቡት ተማሪዎች በርካታ ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ ወደ ኮሌጆች የሚገቡ ሰዎች ደግሞ ዐዋቂ ቢሆኑ እንጂ ክርስቲያን መሆን አይችሉም፡፡ ዐዋቂነትና መራቀቅ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ዓላማ አይደለም፡፡ ለቤተ ክርስቲያን በንባብ ላይ ከሚራቀቀው ዐዋቂ ይልቅ፣ እየተንተባተበ ወልድ ዋሕድ ብሎ የሚመሰክር ኦርቶዶክሳዊ ደቀ መዝሙር ያስፈልጋታል፡፡

በተጨማሪም ወደ ኮሌጆች የሚገቡበት የትምህርት መስፈርት ተመሳሳይ ባለመሆኑ በክፍል ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት ለአንዳንዶቹ የሚጠጥርባቸው ለሌሎቹ ደግሞ የሚመጥናቸው አልሆን ይላል፡፡ ለምሳሌ በኮሌጆች ውስጥ በመደበኛው ዲፕሎማ መርሐ ግብር ከዐሥረኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ዲግሪ ድረስ፣ ከፊደል ተማሪ እስከ መጻሕፍት መምህራን ድረስ አንድ ላይ በአንድ ክፍል የሚማሩበት ዕድል አለ፡፡ ባለዲግሪው በእንግሊዝኛ የሚሰጡ ትምህርቶች ላይ የተሻለ ግንዛቤ ሊኖረው ሲችል፣ ዐሥረኛ ክፍል የጨረሰው ከትምህርቱ በላይ ፈታኝ የሚሆንበት እንግሊዝኛ ቋንቋ ማጥናቱ ይሆናል፡፡ ወደ ግእዝ ቋንቋ ስንመጣም ችግሩ ተመሳሳይ ነው፡፡ የቅኔ እና የመጻሕፍት መምህራን ግእዝን ካልቆጠረው ጋር አብረው ይማራሉ፡፡
፬.የትምህርት አሰጣጥ
ኮሌጆች ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት አብዛኛው ዕውቀት ተኮር እንጂ ምግባር ተኮር አይደለም፡፡ የትምህርት አሰጣጡም ተማሪዎች ጉዳዩን ዐውቀውት ማስተማር እንዲችሉ ማድረግን እንጂ እንዲኖሩት ማድረግን ዓላማው ያደረገ አይደለም፡፡ የነገረ መለኮት ምሩቅ ከሌሎች ሰዎች የሚለየው በዕውቀቱ እንጂ በሕይወቱ እንዲሆን የተሠራው ሥራ አናሳነው፤ ወይም የለም፡፡ ይህ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለግለሰቡ ሕይወት አንዳች ረብ የሌለው መጻሕፍትን ይዞ እንደማይጠቀምባቸው ቤተ መጻሕፍት መሆን ነው፡፡
ትምህርቱም በመምህራን እውነተኛነት፣ ታማኝነትና ክርስትና ላይ የተመሠረተ እንጂ የኮሌጆቹ አስተዳደሮች ስለሚሰጠው ትምህርት የሚያደርጉት ክትትል የለም፡፡ ኮሌጆቹ አንድ መምህር ክፍል መግባት ወይም አለመግባቱን፣ ገብቶ የሚያስተምረው የትምህርት ይዘት ኦርቶዶክሳዊ ዶግማና ቀኖናን የተከተለ መሆን አለመሆኑን የሚቆጠ ጣጠሩበት ሥርዓት የላቸውም፡፡ ይህ ደግሞ ማስተማር መንፈሳዊ አገልግሎት ሳይሆን የገንዘብ ማግኛ ሥራ አድርገው የሚቆጥሩ ብዙ መምህራን እንዲኖሩ የሚያደርግና ያደረገ አሠራር መፍጠር ችሏል፡፡

፭.የተማሪ አያያዝ
ኮሌጆች ምግብ፣ ልብስ፣ መጠለያና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችን አሟልተው በመደበኛው የቀን መርሐ ግብር የሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ባላቸው ትርፍ ጊዜ የት እንደሚሔዱ፣ ምን እንደሚሠሩ፣ ከማን ጋር እንደሚውሉ ወዘተ የሚደረገው ቁጥጥር በጣም የላላ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ትምህርት የማይሰጥባቸውን ዕለታት ተማሪዎች መገኘት ከማይገባቸው አልባሌ ቦታዎች ጀምሮ ወደ መናፍቃን አዳራሽ ሳይቀር ይሔዳሉ፡፡ ለምሳሌ በከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ሲማሩ ከነበሩ የተወሰኑ ተማሪዎች መካከል እሑድ ከዐራት ሰዓት ጀምሮ የሚሔዱበት የመናፍቃን አዳራሽ አለ፡፡ ሰፊ እረፍት ሲኖራቸው ደግሞ አዲስ አበባ እንዲመጡ በማድረግ በአሸናፊ መኮንን ሰብሳቢነት በኮሌጁ ውስጥ ስለሚሠሩት የኑፋቄ ሥራ ሥልጠና ይሰጣቸዋል፡፡ የተለያዩ የመናፍቃን መጻሕፍትን በኮሌጁ ውስጥ በነጻ ያድላሉ፣ “የአሸናፊ መኮንንን መጻሕፍት ያላነበበ ተማሪ የነገረ መለኮት ተማሪ አይባልም” የተባለ እስከሚመስል ድረስ በነፍስ ወከፍ ለሚከተሏቸው ሰዎች ሁሉ ይታደላል፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየው የኮሌጆቹ አስተዳደሮች የሚያስተምሯቸው ሰዎች ሕይወት ገዷቸው የሚሠሩት ሥራ እንደሌለ ነው፡፡

፮.ከወጡ በኋላ ያለው ክትትል ማነስ
ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ከሦስቱም መንፈሳዊ ኮሌጆች ልጆችን ታስመርቃለች፡፡ ነገር ግን በኮሌጆች ውስጥ ቆይተው መውጣታቸውን እንጂ በትክክል የሚገባቸውን ነገር (ዕውቀትን ከሥነ ምግባር አስተባብረው) ይዘው መውጣታቸውን፣ ከወጡም በኋላ በተመደቡበት ሀገረ ስብከት ቤተ ክርስቲያን የምትፈልግባቸውን ያህል እየሠሩ መሆኑን፣ የሚያስተምሩት ትምህርት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት የተከተለ መሆኑን የምታውቅበት ሥርዓት አልዘረጋችም፡፡ እስካሁን ስንት ደቀ መዛሙርት ተመረቁ? ከተመረቁት ውስጥ ስንቶች በአገልግሎት ላይ አሉ?፣ ስንቶች በሃይማኖታቸው ጸንተው፣ በምግባራቸው ቀንተው እያገለገሉ ነው? ስንቶች አገልግሎት አቁመዋል? ስንቶችስ ወደ ሌላ እምነት ገብተዋል? ወደ ሌላ እምነት እንዲገቡ ያደረጋቸው ገፊ ምክንያት ምንድን ነው? አሁን ያሉበት አቋም ምን ይመስላል? የሚሉት ጉዳዮች ለኮሌጆችም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች መሆን አልቻሉም፡፡ ይህ ክፍተት እነሱን መሣሪያ አድርገው ለመጠቀም ሌት ከቀን ለሚተጉት መናፍቃን ጥሩ ዕድል ሆኗ ቸው ውጭ ሆነው ለሚሠሩት የጥፋት ሥራ የውስጥ ዐርበኛ ሆነው የሚያገለግሏቸውኦርቶ-ጴንጤ€ የኮሌጅ ምሩቃን ሰባኪ፣ የስብከተ ወንጌል ሓላፊና የደብር አስተዳዳሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድጓል፡፡

፯.የትኩረት ማነስ
በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ በዓላማና በረቀቀ ዘዴ እየተሠራ ያለውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ መኖሩን ካለመቀበል ጀምሮ እንቅስቃሴውን ለማስቆም የተሠሩ ሥራዎች አለመኖራቸው ለጉዳዩ የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተሐድሶ ማኅበረ ቅዱሳን የፈጠረው የመወደጃ ፍረጃ€ እንጂ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት የተሸረበ ሥውር ሴራ መሆኑን አልተረዱትም፣ ወይም ሊረዱት ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ ይህ አቋም ሁለት ዓይነት ትርጉም ይኖረዋል፡፡ አንደኛው በአስተዳደር ሓላፊነት ላይ ካሉት አካላት ውስጥ ተሐድሶን የሚደግፉ፣ የውስጥ ዐርበኛ ሆነው የሚሠሩና በዓላማ የተሰማሩ ሰዎች አሉ ማለት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ትኩረት የማይሰጡ፣ ክርስትናን በጊዜያዊ ነገር የሚለውጡ፣ የሚነገራቸውን ነገር ላለመስማት ጆሯቸውን የደፈኑ እና ምን እየተሠራ እንደሆነ እንኳን መረጃው የሌላቸው ሰዎች በሓላፊነት ላይ እንደተቀመጡ የሚያስገነዝብ ነው፡፡
እንቅስቃሴው በቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሰው ጉዳት
፩.ሃይማኖታዊና ሥነ ምግባራዊ ችግር
አንድ መናፍቅ ምንም ትምህርት የሌለውን ክርስቲያን ከማታለል ይልቅ ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቀ ሰባኪን ማሳመን ይቀለዋል፡፡ ለዚህም ነው በተሐድሶ መናፍቃን ማኅበራት ውስጥ ከምእመኑ ይልቅ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች ከተመረቁት ደቀ መዛሙርት መካከል የሚበዙት መናፍቅ የሆኑት፡፡ ብዙ ተመራቂዎች እንደሚናገሩት ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቀ ሰው የመጀመሪያ የምስጋና ጸሎቱ €œአቤቱ መናፍቅ ሳልሆን እንድወጣ ስላደረግኸኝ አመሰግንሀለሁ የሚል ነው፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ምሩቅና መናፍቅ አቻ ለአቻ የሚነገሩ ቃላት ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት ንግግሮች መንፈሳዊ ኮሌጆችና €œደቀ መዛሙርቱ€ ምን እና ምን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ እንድንጠይቅ ያስገድዱናል፡፡

ለብዙ የተሐድሶ መናፍቃን መፈጠር፣ ለብዙ ምእመናን ከአገልግሎት መውጣትና ከሃይማኖት መራቅ የዋናውን ድርሻ የሚወስዱት እነዚሁ €œደቀ መዛሙርት€ ናቸው፡፡ ሃይማኖቱን በመተውም ቅድሚያውን የሚይዘውም ያልተማረው ኅብረተሰብ ሳይሆን እነዚሁ ናቸው፡፡ የዚህ ምክንያቱ መጀመሪያ የነበራቸው የትምህርት መሠረት ወይም የትምህርት አሰጣጡ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የመናፍቃኑ የመጀመሪያ €œጥቅሶች€ (ማሳያዎች ማለታችን ነው) መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላት ሳይሆኑ ከእነዚህ መንፈሳዊ ኮሌጆች አፈንግጠው የወጡ ሰዎች ናቸው፡፡ የደቀ መዛሙርቱ በሃይማኖትና በምግባር መውጣት የቤተ ክርስቲያን ችግር ተደርጎ ተወስዶ ለብዙ ምእመናን ከመንገዳቸው ለመውጣት ምክንያት ሆኗል፡፡

፪.ሁሉንም እንዲጠሉ ማድረግ
ከመንፈሳዊ ኮሌጆች ተመርቀው የወጡ በቃልም በሕይወትም የሚያስተምሩ፣ ሃይማኖትና ምግባር እንደ ድርና ማግ አስተባብረው የያዙ የቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች መኖራቸው እውነት ነው፡፡ በገጠር ያለችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲጠናከር አምሳና መቶ ኪሎ ሜትር በእግራቸው እየሔዱ፣ ወጣቶችን እየሰበሰቡና እያስተማሩ ሌት ከቀን የሚደክሙ ደቀ መዛሙርት አሉ፡፡ እንደእነዚህ ያሉ ደቀ መዛሙርት ያሉትን ያህል ደግሞ፣ ከርሳቸው እስከሞላ ድረስ ለሌላው መዳን አለመዳን ግድ የሌላቸው የቤተ ክርስቲያን የብብት እሳት የሆኑም አሉ፡፡ በሥጋና በመንፈስ መግባ ያሳደገቻቸውን ቤተ ክርስቲያን ከጠላቷ ከአርዮስ ጋር ወግነው ሊያፈርሷት የሚሯሯጡ የእናት ጡት ነካሾች በቁጥር እየበዙ መሔዳቸው ምእመናን እውነተኞችን አገልጋዮች እንዲጠራጠሩ፣ ከመጥፎዎቹ ጋር አብረው ደምረው እንዲጠሉ በር እየከፈተ ነው፡፡

፫.የሰውና የገንዘብ ኪሳራ
የቤተ ክርስቲያን ገንዘቧ ሰው እንጂ ብርና ወርቅ አይደለም፡፡ በመምህራን እግር ተተክተው መንጋውን እንዲጠብቁ ለብዙ ዓመታት የደከመችባቸው ልጆቿን ከማጣት በላይ ለቤተ ክርስቲያን ሌላ ኪሳራ የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያጣችው ልጆቿን ብቻ አይደለም፤ ለእነዚህ ሰዎች ያባከነችውን ገንዘብ፣ የሰው ኃይልና ጊዜ ጭምር እንጂ፡፡ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች የሚመረቁ እውነተኞቹ ደቀ መዛሙርት ከመድረኩ ርቀው የቢሮ ሥራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ይህም ለቤተ ክርስቲያን ሁለት መንታ ችግሮችን አስከትሏል፡፡ አንደኛው ቤተ ክርስቲያን ስትለፋባቸው የኖረቻቸው ልጆቿ ዓላማዋን ሳያሣኩላት መቅረታቸው ሲሆን፤ ሁለተኛውና አሳዛኙ ደግሞ ሌሎች የተሐድሶ አቀንቃኞች ቦታውን እንዲይዙት ማድረጉ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ቦታውን መያዛቸው ብቻ ሳይሆን እውነተኞቹ ከመድረኩ ስለጠፉ እነርሱ እውነተኛ መስለው መታየታቸው የበለጠ ቤተ ክርስቲያንን እየጎዳት ነው፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ተሰሚነት ያለው የሚናገር፣ የሚጽፍ ወይም የሚዘምር ሰው ስለሆነ ነው፡፡

የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በሁሉም ኮሌጆች ያለ መሆኑን ከየኮሌጆቹ በተለያዩ ጊዜያት የተባረሩ የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኞች፣ ምክርና ተግሣጽ ተሰጥቷቸው የቀጠሉ ተማሪዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡ እንቅስቃሴው በሦስቱም መንፈሳዊ ኮሌጆች ያለ ነው፡፡ በየኮሌጆቹ ማሳያዎችን በመጥቀስ ጉዳዮችን ማብራራት ተገቢ ይሆናልና ወደዚያ እንለፍ፡፡

ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አዲስ አበባ መሆኑና መንፈሳዊ ኮሌጆች ላይ መሠረት አድርጎ የሚሠራውን የውጪውን የተሐድሶ መናፍቃን ድርጅትም ትኩረት የሳበ በመሆኑ ብዙ እንቅስቃሴዎች ይደረጉበታል፡፡ ከውጪ እስከ አገር ውስጥ መረባቸውን የዘረጉ የተሐድሶ መናፍቃን ድርጅ ቶች ሰፋ ያለ መሠረት ለመጣል ሲሞክሩ ነበር፣ አሁንም እየሠሩ ነው፡፡ እንቅስቃሴው በአብዛኛው የቀን መደበኛ ተማሪዎችን ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ከኮሌጁ ተመርቀው በተሐድሶ መናፍቃን መረብ ውስጥ ያሉ ደቀ መዛሙርት€ አሉ፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ በትምህርት ላይ ያሉ ወደ መናፍቃን አዳራሽ የሚሔዱ፣ ከአሸናፊ መኮንን ጋር የሚማሩ ብዙ ተማሪዎች አሉ፡፡ ፳፻ወ፮ ዓ.ም ላይ ቁጥራቸው ዐሥር የሚደርሱ ተማሪዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን የሚነቅፍና የክህደት ትምህርት ሲያሠራጩ በኮሌጁ ደቀ መዛሙርት መረጃ ቀርቦባቸዋል፡፡ ጉዳያቸውም ለኮሌጁ ቀርቦ እየታየ ሲሆን፤ የድምጽና የሰው ማስረጃ የቀረበባቸው የኑፋቄ ትምህርቶቻቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡

፩.አማላጃችን ኢየሱስ ነው እንጂ ሌላ አማላጅ የለም፤
፪.በጸጋው አንዴ ድነናል፣ ስለዚህ ሥራ ለምስክርነት ነው እንጂ ለመዳናችን ምንም አያስፈልግም፤
፫.ኅብስቱ መታሰቢያ ነው እንጂ፣ ሕይወት የሚሰጥ አማናዊ የጌታ ሥጋና ደም አይደለም፤
፬.ለፍጡር አድኅነኒ አይባልም፣ ማርያም አታድንም፤
፭.በጸሎት ቤት ስለ ድንግል ማርያም ክብር ትምህርት ሲሰጥ “ተረታ ተረትህን ተውና ውረድ” ብሎ መቃወም፤
፮.ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ መላእክት እያልን ወንጌልን አንሸቃቅጥ፤
፯.ጻድቃን ሰማዕታት፣ መላእክት አያማልዱም፣ አያድኑም፣ አያስፈልጉም፣ አንድ ጌታ አለን፤
፰.ለቅዱሳን ስግደት አይገባም፣ የአምልኮ እንጂ የጸጋ የሚባል ስግደት የለም፤
፱.ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አትሰብክም፣ የምትሰብከው ፍጡራንን ነው፤
፲.ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸው መጻሕፍት በሙሉ ኮተቶች ናቸው፤
፲፩.እኛ የሐዲስ ኪዳን ልጆች ነን የአንድምታ መጻሕፍት አያስፈልጉንም፤
፲፪.በሐዲስ ኪዳን ካህን አያስፈልግም፣ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ ንስሐም መናገር ያለብን ለጌታ ብቻ ነው፤
፲፫.በጳጳሳት፣ በመነኮሳት፣ በቀሳውስት፣ በዲያቆናት እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በሚያስተምሩትና በሚማሩት፣ በሚጾሙትና በሚያስቀድሱት የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ላይ ጸያፍ ስድብና ዘለፋ መናገር፡፡ ከሚናገሯቸው የስድብ ቃላት ውስጥ፡- ግብዞች፣ በጨለማ የሚኖሩ፣ ዶማዎች፣ ደንቆሮዎች፣ ያልበራላቸው፣ የጌታ ጠላቶች፣ ወዘተ ይገኙበታል፡፡
፲፬.ታቦት ጆሮ ስለሌለው አይሰማም፣ ስለዚህ አያስፈልግም ፣
፲፭.ሕዝቡን ለብዙ ሺሕ ዘመናት ለጣዖት ስናሰግደው ኖረናል፣
፲፮.አሁን ካለንበት የጨለማ ጫካ መውጣት አለብን፣
፲፯.ቤተ ክርስቲያን፡- ዘረኝነትንና ጽንፈኝነትን ታስፋፋለች፣ የተወሰነ ጎሳ ናት፣
፲፰.አንደኛ ዓመት ተማሪዎችን ሲያገኟቸው €œቲዮሎጂ መማር ከፈለግህ የበላኸውን መትፋት አለብህ€፣ ወዘተ በማለት መዝለፍና ክፉ ምክር መምከር የሚሉት ናቸው፡፡

ይህ የሚያሳየው ከዚህ ኮሌጅ ተመርቀው የተሐድሶ መናፍቃኑን ጎራ የተቀላቀሉት ሰዎች ኮሌጁን በሚፈልጉት መልኩ ለመቅረፅ ሰፋ ያለ ሥራ እየሠሩ መሆኑን ነው፡፡ ይህም ፍሬ ኮሌጁ በእነዚህ ደቀ መዛሙርት ላይ እንደሆነው በየጊዜው እያጠራ ካልሔደ ችግሩን ውስብስብ እና ከባድ ያደርገዋል፡፡

ሌላኛው ኮሌጅ የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኞች “ብዙ ሰዎችን ያፈራንበት ቤታችን ነው ብለው በድፍረት የሚናገሩለት” ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ነው፡፡ ተሐድሶዎችና መናፍቃኑ ከዚህ ኮሌጅ ተመርቆ ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ መገኘት የተአምር ያህል የሚቆጠር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ እነርሱም ከዚህ ኮሌጅ የተመረቀ መሆኑን ያረጋገጡትን ሰው በልበ ሙሉነት ይቀበላሉ፡፡ በኮሌጁ የኑፋቄው ጠንሳሽ መሠረት ስብሐት ለአብ ነው፡፡ የእርሱን ፈለግ ተከትለው ብዙ ጥፋት ያደረሱት ደግሞ በ፳፻ወ፬ ዓ.ም ተወግዘው የተለዩት ጽጌ ሥጦታውና ግርማ በቀለ ናቸው፡፡ ከ፲፱፻፺ ዓ.ም ጀምሮ የተከሉት እሾህ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያንን እያደማ ይኖራል፡፡ ከዚህ ኮሌጅ ተመርቀው አንዳንዴ ፕሮቴስታንት፣ ሌላ ጊዜ ሙስሊም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ኦርቶዶክስ ሆነው የሚተውኑ ደቀ መዛሙርት€ አሉ፡፡

ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በተሐድሶ መናፍቃን ብዙ ተጽእኖ የደረሰበት ኮሌጅ ነው፡፡ ለብዙ ዓመታት በኮሌጁ እንደ ሐሰተኛ የሚቆጠሩትና አንገታቸውን ደፍተው የሚሔዱት የነበሩት ኦርቶዶክሳውያን ነበሩ፡፡ ይህ የሆነው በሓላፊነት ላይ የነበሩት መሪዎች ድጋፍ የሚሰጡት ከትክክለኞቹ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ይልቅ ለተሐድሶ መናፍቃኑ ስለ ነበር ነው፡፡ ይህ የሆነውም እንቅስቃሴውን የሚደግፉ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ስለሚያግዟቸው ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ ለውጦች እየታዩበት ነው፡፡ የዚህ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተሐድሶ ጠንሳሽ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የመቀሌ ቅርንጫፍ ሰብሳቢ የነበረ ሰው ነው፡፡ አዳዲስ ተማሪዎች ሲገቡ አጥምደው ወደ ቡድናቸው ያስገቡ ነበር፡፡ በ፳፻ወ፮ ዓ.ም ያለውና በዛብህ የሚባሉ ቀንደኛ የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኞች ከዚህ ኮሌጅ ኑፋቄያቸው ተደር ሶበት ተባረዋል፡፡

የተሐድሶ መናፍቃን ተላላኪ የሆኑት የኮሌጁ ተማሪዎች በዕረፍት ሰዓታቸው ወደ አዲስ አበባ መጥተው በአሸናፊ መኮንን አስተባባሪነት ይሰበሰባሉ፡፡ ለቡድናቸው አባላት መጽሐፍ ቅዱስ፣ የአሸናፊ መኮንን መጻሕፍት እና ሌሎችም ተሐድሶዎች የጻፏቸው መጻሕፍት ይታደላሉ፡፡ ፳፻ወ፯ ዓ.ም ላይ በኮሌጁ ተማሪዎች በተደረገ የመረጃ ማጠናቀር የተደረሰበት በኮሌጁ ከሚማሩት ተማሪዎች ውስጥ ሃምሳ በመቶ ያህሉ ተሐድሶዎችና የተሐድሶ መናፍቃን ደጋፊዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የኮሌጁ ተማሪዎች ግንባር ቀደም የተሐድሶ አንቀሳቃሾች ናቸው፡፡

ስለ መንፈሳዊ ኮሌጆች ስንናገር መንፈሳዊ ኮሌጆች በእምነት የጸኑ፣ በምግባር የቀኑ ደቀ መዛሙርትን አላፈሩም ማለታችን አለመሆኑን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ከተመሠረቱበት ዓላማ አንጻር የምርቱን ያህል ግርዱም እየበዛ ማስቸገሩን ለማሳየት አቅርበናል፡፡ እንኳን ትልቅ ተቋም አንድ ግለሰብም የወለዳቸው ልጆች ሁሉ መልካሞች፣ ያስተማራቸው ተማሪዎች ሁሉ ዐዋቂዎች ወይም መንፈሳውያን እንደማይሆኑለት ይታወቃል፡፡ ይህ የነበረ፣ ያለና የሚቀጥል እውነት ነው፡፡ ከጌታችን እግር ሥር ቁጭ ብለው ከተማሩት ሐዋርያት መካከል ይሁዳ በስንዴ መካከል የበቀለ እንክርዳድ ነበር፤ በተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ እግር ሥር ቁጭ ብለው ከተማሩት ደቀ መዛሙርት መካከልም አርዮስ በቅሏል፡፡

ነገር ግን በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ እየታየ ያለው ንጹሕና የተቀላቀለ ስንዴ አስገብቶ እንክርዳድ የማምረቱ ጉዳይ እየጨመረ መምጣቱን አህጉረ ስብከትም እየገለጡ ነው፡፡ እዚህ ላይ ለማስገንዘብ የምንፈልገውም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አቅሟን የምታጠናክርባቸው፣ ተተኪ ሊቃውንትን የምታፈራባቸው መንፈሳዊ ካሌጆች፤ የተሐድሶ መናፍቃን መፈልፈያ ለማድረግ በዓላማ ሌት ከቀን እየተሠራ ያለውን ተግባር ምን ያህል አውቀነዋል በሚል እንጂ፤ በየኮሌጆቹ ውስጥ ሆነው አቅማቸው በፈቀደ፣ ይህን ሥውር ደባና ዘመቻ ለማጋለጥ የሚተጉ ደቀ መዛሙርት የሉም ለማለት አይደለም፡፡፡ ሆኖም ግን ተፅዕኖውና ዘመቻው ከእነሱ አቅም በላይ ስለሆነ፤ በመዋቅሩ ደረጃ ችግሩን ለመቅረፍ መሠራት የሚኖርባቸውን ተግባራት ለማመላከትና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች የሆኑ በየኮሌጆቹ የሚገኙ ደቀ መዛሙርትም በፅናት ሆነው የተሐድሶ መናፍቃን ዓላማ ግቡን እንዳይመታ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉ ለማሳሰብ ነው፡፡

እውነተኞቹ ደቀ መዛሙርት እኩይ ተግባራቸውን ስለገለጡባቸው ተሐድሶ መናፍቃንም ተነካን በሚል የዋሃንን አስተባብረው ለመጮህ ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸውን ለማስገንዘብ ነው፡፡ ስለዚህ ደግመን እንጠይቃለን መንፈሳዊ ኮሌጆችና €œደቀ መዛሙርት ምን እና ምን ናቸው?€ ይህንን የምንለው ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮች ተቀርፈው ኦርቶዶክሳውያን ደቀ መዛሙርት እንዲበዙና ወጥተውም በተማሩት ሙያ እንዲያገለግሉ የሚያ ደርግ ሥራ መሥራት እንደሚገባን ለማመልከት ነው፡፡

No comments:

Post a Comment