ከክፍል ሰላሳ ስምንት የቀጠለ፦
የተከበራችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት
ተዋሕዶ ልጆች!
እንኳን ለእናታችን ለወላዲተ አምላክ
ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የቃል ኪዳን በዓል አደረሳችሁ አደረሰን፡፡
ከዚህ በመቀጠል ስለ እመቤታችን ክብር ተናግረው የማይጠግቡት፤በተለይም
ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን በመተርጎምና የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሁላችንም በየቤታችን እንድንሰማውና እንድንማርበት እንድንቀደስበትም
በሲዲ አዘጋጅተው ያበረከቱልን መምህራችን ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ደምፀ፤ የእመቤታችንን የኪዳነ ምሕረት በዓል በማስመልከት በማሕበራዊ
ድረ-ገጽ ያስተላለፉትን ትምህርት ከዚህ ቀጥሎ አቅርበንላችኋል፡፡