ከክፍል ሰላሳ ሰባት የቀጠለ፦
የተወደዳችሁ አንባብያን! እንኳን የካቲት አምስት ቀን 2010 ዓ.ም ለምንጀምረው ዐቢይ ጾም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን፡፡
ከዚህ በመቀጠል ስለ ዐቢይ ጾም መጠነኛ ግንዛቤ የምናገኝበት ትምህርት፤እንዲሁም
በዐቢይ ጾም ውስጥ በሚውሉት ስምንት ሰንበታት /እሑዶች/ በቅዳሴ
ጊዜ የሚነበቡትን ምንባባት በተመለከተ በዝርዝር አቅርበንላችኋልና በጥሞና እንድትከታተሉት እንጋብዛለን፡፡
ስለ ዐቢይ ጾም የተዘጋጀ አጭር ትምህርት
ዐቢይ ጾም
“ዐቢይ”የሚለው ቃል የግዕዝ ቃል ሲሆን “ዐበየ” ማለት “ከፍ አለ”፣“ታላቅ
ሆነ” ማለት ነው፡፡ከዚህም ግስ “ዐቢይ” የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡
ይህ ጾም ዐቢይ የተባለበት ምክንያት፡-
ሀ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ፤
ለ. በቀኑ ብዛት ከሌሎች አጽዋማት
የሚበልጥ ስለሆነ፤
ሐ. ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች
ማለትም “ስስት” “ትዕቢት” “ፍቅረ ነዋይ” ድል የተመቱበት ስለሆነ
ነው፡፡እነዚህም አርዕስተ ኃጣውእ /የኃጢአት መሠረቶች/ በመባል ይታወቃሉ፡፡
ስስት ፦
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርባውን ቀን ጾሞ ሲፈጸም ተራበ::
በዚህ ጊዜ ጠላት ሰይጣን “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው”::ጌታችንም መልሶ “ሰው ከእግዚአብሔር
አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፏል” በማለት በስስት የመጣውን ፈተና በትዕግስት ድል አድርጎታል፡፡
ትዕቢት ፦
ለሁለተኛ ጊዜ ጠላት ሰይጣን “መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም
በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ወደ ታች ራስህን ወርውር” በማለት
ላቀረበለት ፈተና ጌታችን “ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፏል” ብሎ በትዕቢት የመጣውን ፈተና በትህትና አሳፍሮ
መልሶታል፡፡
ፍቅረ ነዋይ ፦
ለሦስተኛ ጊዜ ጠላት ሰይጣን “የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም
አሳይቶ፦ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው፡፡”ያን ጊዜ ጌታችን “ሂድ አንተ ሰይጣን፤ ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም
ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና ” በማለት የዚህን ዓለም ሀብትና ንብረትን በመውደድ የመጣውን ፈተና ሀብትና ንብረትን በመጥላት(በጸሊዓ
ንዋይ) ድል አድርጎ፤ለእኛም የድል ማድረጊያውን መሣሪያ እንዲህ በማለት አስረክቦናል"በዓለም ሳላችሁ መከራ አለበችሁ፤ነገር
ግን አይዟችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ::" (ዮሐ.ም.፲፮ ቁ.፴፫፡)
ትምህርቱን በሚገባ ለመረዳት የሚከተለውን
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይመልከቱ፡፡ ማቴ.ም.፬ ቁ.፩-፲፩፣ ማር.ም.፩፣ቁ.፲፪-፲፫፣ ሉቃ.ም.፬ ቁ.፩-፩፫ ፡፡
በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት( እሑዶች) እያንዳንዳቸው
ስያሜ አላቸው እነርሱም፡-
፩ኛ. ዘወረደ፦
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን፤ ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ፤
ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ አልፋና ኦሜጋ የሆነው ዘለዓለማዊው አምላክ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና
ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ስያሜ ነው፡፡
፪ኛ. ቅድስት፦
ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን “ቅድስት” የተባለበትም ምክንያት፤ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ የሚመሰገን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾምን የቀደሰበት/ የባረከበት/ ሳምንት ስለሆነ ነው፡፡
፫ኛ. ምኩራብ፦
ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን፤ በዚህ ዕለት መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አይሁድ ቤተ መቅደሱን መሸጫና መለወጫ
አድርገውት ስለነበር፤ከዚህ አላስፈላጊ ድርጊት ቤተ መቅደሱን ያጸዳበት ዕለት መሆኑ ይታሰብበታል፡፡
፬ኛ. መጻጉዕ ፦
ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን፤ በዚህ ዕለት ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ፣ እውራንን ማብራቱ፣ ለምጻሞችን ማንጻቱ፣ ሽባዎችን መተርተሩ፣ በዋናነት የሰላሳ ስምንት ዓመቱን በሽተኛ
አልጋውን ተሸክሞ እንዲሄድ ማድረጉን፤ እነዚህ ሁሉ ድንቅ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው፡፡
፭ኛ. ደብረ ዘይት፦
ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ
የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡ዳግመኛ በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ እንደሚመጣ የሚታሰበውም በዚህን ዕለት ነው፡፡ማቴ.ም.፳፭ ቁ.፴፩
፮ኛ. ገብር ኄር፦
ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና
በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው፡፡
፯ኛ. ኒቆዲሞስ፦
ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው
የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል፡፡ በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ
የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡
፰ኛ. ሆሳዕና፦
ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት
መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ላይ
ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብሎ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት
መድኃኒት ማለት ነው፡፡ በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሐት ስለማይፈጸም ለምእመናን ሁሉ ጸሎተ ፍትሐት የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::
ጾማችንን በተገቢው መንገድ ፈጽመን፤ለነፍሳችንም ሆነ ለሥጋችን በረከት የምናገኝበትና ብርሃነ ትንሣኤውን በመንፈሳዊ ሐሴት የምናከብርበት መልካም ጊዜ እንዲሆንልን፤የአምላከ
ቅዱሳን የልዑል እግዚአብሔር ቸርነቱ፤ የወላዲተ አምላክ የቅድስት
ድንግል ማርያም የእናት አማላጅነቷ፤ የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡
ከዚህ በመቀጠል የ፳፻፲ ዓ.ም የዓቢይ ጾም እሑዶች የሚውሉበትን
ቀንና የየለቱን ምንባባት ይመልከቱ፡፡የንባባቱ ማውጫ የተወሰደው ከመጽሐፈ ግጻዌ ገጽ ፻፴፩-፻፴፫ ሲሆን፤ እንደ አስፈላጊነቱ በሊቃውንቱ ውሳኔ ምንባባቱም ሆነ
ቅዳሴው በየዕለቱ ሊቀያየሩ ይችላሉ፡፡
የዕለቱ ስያሜ
|
ቀኑ
|
ምንባብ
|
ምንባባቱ የሚገኙበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
|
ዘወረደ
|
የካቲት ፬
|
፩ኛ ምንባብ
|
ዕብራውያን ም.፲፫ ቁ.፯
|
፪ኛ ምንባብ
|
ያዕቆብ ም. ፬ ቁ. ፮
|
||
፫ኛ ምንባብ
|
የሐ.ሥራ ም.፳፭ ቁ.፲፫
|
||
ምስባክ
|
ተቀነዩ ለእግዚአብሔር
በፍርሃት
|
||
ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ
|
|||
አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ
ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር
|
|||
ወንጌል
|
ዮሐንስ ም.፫ ቁ.፲
|
||
ቅዳሴ
|
ዘእግዚእነ
|
||
ቅድስት
|
የካቲት ፲፩
|
፩ኛ ምንባብ
|
፩ኛ ተሰ.ም.፬ ቁ.፩
|
፪ኛ ምንባብ
|
፩ኛ ጴጥ.ም.፩ቁ. ፲፫
|
||
፫ኛ ምንባብ
|
የሐ.ሥራ ም.፲ቁ.፲፯
|
||
ምስባክ
|
እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ
|
||
አሚን ወሰናይት ቅድሜሁ
|
|||
ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ
|
|||
ወንጌል
|
ማቴ.ም.፮ ቁ.፲፯
|
||
ቅዳሴ
|
ዘኤጲፋንዮስ
|
||
ምኩራብ
|
የካቲት ፲፰
|
፩ኛ ምንባብ
|
ቆላስዪስ ም.፪ ቁ. ፲፯
|
፪ኛ ምንባብ
|
ያዕ.ም.፪ ቁ. ፲፬
|
||
፫ኛ ምንባብ
|
የሐ፣ሥራ ም.፲ ቁ.፩
|
||
ምስባክ
|
እስመ ቅንአተ ቤትከ በልዐኒ
|
||
ትዕይርቶሙ ለእለይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
|
|||
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ
|
|||
ወንጌል
|
ዮሐ.ም.፪ ቁ. ፲፪
|
||
ቅዳሴ
|
ዘእግዚእነ
|
||
መፃጒዕ
|
የካቲት ፳፭
|
፩ኛ ምንባብ
|
ገላ.ም.፭ ቁ. ፩
|
፪ኛ ምንባብ
|
ያዕ.ም.፭ ቁ. ፲፬
|
||
፫ኛ ምንባብ
|
የሐ.ሥራ.ም.፫ ቁ. ፩
|
||
ምስባክ
|
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
|
||
ወይመይጥ ሎቱ ምስካቤሁ እምደዌሁ
|
|||
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ
|
|||
ወንጌል
ቅዳሴ
|
ዮሐ.ም.፭ ቁ. ፩
ዘእግዚእነ
|
||
ደብረ ዘይት
|
መጋቢት ፪
|
፩ኛ ምንባብ
|
፩ኛ ተሰሎንቄ ም.፬ ቁ. ፲፫
|
|
|
፪ኛ ምንባብ
|
፪ኛ ጴጥ.፫፤፯
|
|
|
፫ኛ ምንባብ
|
የሐ.ሥራ.ም.፳፬ ቁ.፩
|
|
|
ምስባክ
|
እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ
|
|
|
|
ወአምላክነሂ ኢያረምም
|
|
|
|
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ
|
|
|
ወንጌል
|
ማቴ.ም.፳፬ ቁ.፩
|
|
|
ቅዳሴ
|
አትናቴዎስ
|
ገብር ኄር
|
መጋቢት ፱
|
፩ኛ ምንባብ
|
፪ኛ ጢሞ.ም.፪ ቁ.፩
|
|
|
፪ኛ ምንባብ
|
፩ኛ ጴጥ.ም.፭ ቁ.፩
|
|
|
፫ኛ ምንባብ
|
የሐ.ሥራ.ም.፩ ቁ.፮
|
|
|
ምስባክ
|
ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ
|
|
|
|
ወሕግከኒ በማዕከለ ከርስየ
|
|
|
|
ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ
|
|
|
ወንጌል
|
ማቴ.ም.፳፭ ቁ.፲፬
|
|
|
ቅዳሴ
|
ዘባስልዮስ
|
ኒቆዲሞስ
|
መጋቢት ፲፮
|
፩ኛ ምንባብ
|
ሮሜ ም.፯ ቁ.፩
|
|
|
፪ኛ ምንባብ
|
፩ኛ ዮሐ.ም.4 ቁ.፲፰
|
|
|
፫ኛ ምንባብ
|
የሐ.ሥራ.ም.፭ ቁ.፴፬
|
|
|
ምስባክ
|
ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ
|
|
|
|
አመከርከኒ ወኢተረክብ በዓመጻ በላዕሌየ
|
|
|
|
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓለ እመሕያው
|
|
|
ወንጌል
|
ዮሐ.ም.፫ ቁ. ፩
|
|
|
ቅዳሴ
|
ዘእግዝእተነ
|
ሆሣዕና
|
መጋቢት ፳፫
|
፩ኛ ምንባብ
|
ዕብ.ም.፱ ቁ. ፲፩
|
|
|
፪ኛ ምንባብ
|
፩ኛ ጴጥ.ም.፬ ቁ.፩
|
|
|
፫ኛ ምንባብ
|
የሐ.ሥራ.ም.፳፰ ቁ. ፲፩
|
|
|
ምስባክ
|
እምአፈ ደቂቅ ወሕጻናት አስተዳሎከ ስብሐተ
|
|
|
|
በእንተ ጸላዒ
|
|
|
|
ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ
|
|
|
ወንጌል
|
ማቴ.ም.፳፩ ቁ. ፩
|
|
|
ቅዳሴ
|
ዘጎርጎርዮስ
|
No comments:
Post a Comment