የተወደዳችሁ
አንባብያን!
ቀደም ብለን ባስነበብናችሁ ሁለት ክፍሎች የቤተ ክርስቲያን ሳይሆኑ በተለያየ መንገድ የቤተ ክርስቲያን መስለው ስለሚያሳስቱ መናፍቃን የተወሰነ ግንዛቤ ለማሰጨበጥ ሞክረናል፡፡ሆኖም ዋና ዋናውን ጥፋታቸውን ለማመላከት ያህል ነው እንጂ የማሳሳቻ ስልታቸው ይህ ብቻ ነው ማለት አይደለም ፡፡ከሚናገሩትና ከሚጽፉት በተጨማሪ ዲያቆን ፣ካህን፣መነኩሴ፣ሰባኬ ወንጌል፣ወ.ዘ.ተ.መስለው ለማሳሳት ካባውን፣ቆቡን፣መስቀሉንና ቀሚሱን ለብሰው ከበሮውን፣ ጸናጽሉን፣መቋሚያውንና የመሳሰለውን የቤ/ክ ንዋያተ ቅድሳት ይዘው በተለያዩ የሕዝብ መገናኛዎች ሳይቀር /የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጨምሮ/ የሐሰት ትምህርታቸውን በቤተ ክርስቲያናችን ስም ያስተላልፋሉ፡፡እኛ የተዋህዶ ልጆች የእኛና የእነሱ የሆነውን ለመለየት ነቅተንና ተግተን እራሳችንንም ሆነ ቤተ ክርስቲያናችንን ከስህተቱ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡
ከፍሬያቸው
ታውቋቸዋላቸሁ
ከላይ በመግቢያችን ላይ በጠቀስነው ወንጌል በጎችንና ተኩላዎችን መለየት የሚንችለው በሚሰሩት ሥራ እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ከዚህ በመቀጠል ከእኩይ ሥራቸው አንዱ የሆነውንና በእነሱው ከሚዘጋጁት የተለያዩ መጽሐፎቻቸው አንዱ የሆነውን “የአዲሰ ኪዳን መካከለኛ ” የተባለውን መጽሐፋቸውን እኛ ደግሞ “‹‹የአዲሰ ኪዳን መካከለኛ» በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘን ” በሚል ርዕስ እናየዋለን፡፡