በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን::
“የበግ ለምድ
ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ፡፡ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ፡፡ ከእሾህ ውይን ክኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን ? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፡፡ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል፡፡”ማቴ.7፤15-18
ይህንን ኃይለ
ቃል የተናገረው ጌታችን አምላካችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ በዚህ ክፍለ ትምህርት ጌታችን ተጠበቁ ፣ተጠንቀቁ ብሎ ያስተማረን እውነተኞቹን በጎች
መስለው በበጎቹ መንጋ ውስጥ የተቀላቀሉትን ተኩላዎች መለየት እንድንችል ሲሆን የማንነታቸው መለያው የስራ ፍሬያቸው እንደሆነ ገልጾልናል፡፡ስለዚህ የሰውን ልቡና መርምሮ የሚያውቀው ልዑል እግዚአብሔር ብቻ ሲሆን እኛ ግን ማንንም ሰው የሚናገረውንና የሚሰራውን አይተንና ሰምተን ምንነቱን ማወቅ እንችላለን ማለት ነው፡፡ስለሆነም በዚህ ሐሰት በነገሰበት፤እውነትና እውነተኛ በጠፋበት አሰጨናቂ ዘመን መናፍቁን ከእውነተኛው አማኝ ለይተን እራሳችንንና ሌላውንም ከክህደትና ከኑፋቄ መጠበቅ ፤ከአባቶቻችን የተረከብናትን በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጸችውን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችን እምነቷ፣ሥርዓቷና ትውፊቷ ሳይፋለስ ለቀጣዩ ትውልድ እንድትተላለፍ ማድረግ የሁላችንም መንፈሳዊ ግዴታ ስለሆነ ከማንኛውም ጊዜ በላይ በሃይማኖትም ሆነ በምግባር ጠንክረን መገኘት ያለብን ጊዜው አሁን እንደሆን ማስተዋል ይገባናል፡፡
ሁላችንም እንደምናየውና
እንደምናውቀው በዓለማችን ውስጥ አንድ ዓይነት መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው እንደየራሳቸው ስሜት እየተረጎሙ የየራሳቸውን የእምነት ድርጅት አቋቁመው
በመሰላቸው መንገድ የሚያመልኩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የክርስቲያን የእምነት ድርጅቶች አሉ፡፡ማንም ሰው በተፈጥሮ የተሰጠውን ነጻ ፈቃድ ተጠቅሞ የፈለገውን ለማምለክ የሚከለክለው ነገር ባይኖርም አንድ እግዚአብሔር፣ አንድ ሃይማኖት/የክርስትና/፣አንድ ጥምቀት የሚል መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ የእምነቱ ዓይነት ብዙ መሆኑ ግን የሁሉንም እምነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል፡፡የበለጠ የሚገርመው ደግሞ እያንዳንዱ የእምነት ድርጅት ከራሱ እምነት ውጪ ያሉትን ሁሉ እንደ ኢአማኒ በመቁጠር የራሳቸውን እያሞጋገሱ የሌላውን እያረካከሱ ድርጅታቸውን ለማስፋፋት የሚያደርጉት ሩጫ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ለእምነት ድርጅታቸው ስያሜ ሰጥተውና የአምልኮ ሥፍራቸውን ለይተው እስካመለኩ ድረስ ትክክል ነው ብሎ ያመነበት በፈቃዱ ይከተላቸዋል ፡፡ከነዚህ ሁሉ የበለጠ የሚያስቸግረው ግን የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሳይሆኑ መስለው ሚያሳስቱን የሐሰት መምህራን ስለሆኑ ከጾምና ከጸሎት ጋር ነቅተንና ተግተን እራሳችንንም ሆነ ቤተ ክርስቲያናችንን መጠበቅ አለብን፡፡

በኛ ዘመን
ያሉት የበግ ለምድ ለብሰው በተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአገልግሎት ዘርፎች ተሰግስገው የኑፋቄ ትምህርታቸውን እንክርዳድ እየዘሩ የሚገኙት በስመ ተሐድሶ የሚንቀሳቀሱ ክፍሎች ናቸው፡፡ስለነዚህ ክፍሎች የጥፋት ተልእኮ ቢያንስ ከሃያ ዓመት ላላነሰ ጊዜ ሲነገር የቆየ ስለሆነ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጅ ሆኖ ይህንን የማያውቅ አለ ብዬ አልገምትም፡፡ይሁን እንጂ ለማስመሰል ብለው ከሚናገሩት አባባል ለምሳሌ “ እኛ ቤ/ክ እንወዳታለን ግን መስተካከል ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ ” እያሉ ሲናገሩ ለአንዳንድ ጉዳዩን በጥልቀት ለማያወቁ ምዕመናን እውነትም ለቤ/ክ በመቆርቆር የተናገሩ ሊመስል ይችላል፡፡በተለይም ዋናው ስልታቸው የሰውን ደካማ ጎን ማጥናትና በዚያው በሚሸነፍበት መንገድ ገብተው ወደራሳቸው የምንፍቅና አዘቅት ማስገባት ስለሆነ እውነተኛ ሳይሆኑ መስለው ያሳሳቷቸው ሰዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡
ወደ ዋናው
ጉዳያችን ስናቀና የዚህ የመወያያ መድረክ ዋና ዓላማ እነዚህ እውነትን እንሰብካልን የሚሉ ነገር ግን የእውነት ጠላቶች የሆኑት ክፍሎች የለበሱትን የማስመሰያ የበግ ለምድ ገፎ ተኩላነታቸውን ማሳየት ነው፡፡ይህንን የማታለያ ለምዳቸውን የሚገልጡባቸው እራሳችው የሚያዘጋጇቸው በራሪ ጽሁፎች ፣ ጋዜጦች ፣መጽሐፎች ፣በተለያየ ጊዜና በተለያየ መድረክ ያስተላፉት ትምህርት ነው፡፡ልዑል እግዚአብሔር በፈቀደልን መጠን ከጽሁፎቻቸው አንዳንድ ኃይለ ቃሎችን እያወጣን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር ምንኛ እየተቃረኑ እንደሆነ እናሳያቸዋለን፡፡እኛ እንደነሱ በሐሰት የሰውን ስም ለማጥፋትና ተሳዳቢውን ለማይጠቅም የሚሰደበውንም ለማይጎዳ ለስድብ ቦታ የለንም፡፡የምንቃወመውም መጥፎ ስራቸውን ነው እንጂ እነሱማ ቀድሞ በተፈጥሮ ወንድሞቻችን እህቶቻችን ስለነበሩ ወደፊትም በንስሃ ከተመለሱ በሃይማኖት ወንድሞቻችን እህቶቻችን ስለሚሆኑ እንወዳቸዋለን፡፡እነሱ ሲሰድቡን እኛ እንመርቃቸዋለን፡፡ጌታችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን፡፡ “.....ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግሙአችሁንም መርቁ......” ፡፡ማቴ.5፤44
ለዛሬው
ይቆየን፡፡
ይቀጥላል፡፡
No comments:
Post a Comment