Saturday, February 21, 2015

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ፡፡” ማቴ.7፤15 ክፍል አምስት

የተወደዳችሁ አንባብያን!
እንደምን ሰነበታችሁ ?
ባለፈው በክፍል አራት ጽሁፋችን የካህናትን አገልግሎት በሚመለከት ጽሁፍ እንመለሳለን ባልነው መሰረት እነሆ ዛሬ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ካቆምንበት “‹‹የአዲሰ ኪዳን መካከለኛ» በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘን ” ብለን በጀመርነው ርዕስ  እንቀጥላለን፡፡
  1.  ከመጽሐፉ ከገጽ 8 የተወሰደ ፦ ‹‹…ዛሬም በሰው ሥርዓት የተሸሙትን ምድራውያን ካህናት አልፈን በመምጣት እግዚአብሔር በሾመው ሰማያዊ ሊቀካህን እግር ሥር እንውደቅ፤ምሕረትም እናገኛለን፡፡››
  2. ከመጽሐፉ ከገጽ 12 የተወሰደ   ‹‹…በመሆኑም በወንጌል ቃል ለተገለጠው እውነት ታማኝ ሊሆኑ ባልቻሉት በዘመናችን አሮኖችና ኤሊዎች መገልገልን ትተን በሰማያዊት መቅደስ እግዚአብሔር ወዳስቀመጠልን ወደታመነው ሊቀካህናት ወደ ኢየሱስ ዘንድ ልንኮበልል ያሰፈልጋል፡፡››
  3. ከመጽሐፉ ከገጽ 17 የተወሰደ ‹‹ከክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ከሐዋርያት ወደ ተከታዮቻቸው እየተባለ ሲወርድ ሲዋረድ እስከ ዘመናችን የደረሰ የተለየ የክህነት መስመር የለም፡፡››
በማለት ለጻፉት ክህደታቸው ምላሽ የሚሆኑትን የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንመልከት

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ፡፡” ማቴ.7፤15 ክፍል አራት

ከቁጥር ሦስት የቀጠለ
የተወደዳችሁ አንባብያን!
እንደምን ሰነበታችሁ ?
ባለፈው በክፍል ሦስት ጽሁፋችን ‹‹እኔ  መንገድና  እውነት ሕይወትም ነኝ...›› በሚለው ርዕስ እንመለሳለን ባልነው መሰረት እነሆ ዛሬ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ካቆምንበት “‹‹የአዲሰ ኪዳን መካከለኛ» በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘን ” ብለን በጀመርነው ርዕስ  እንቀጥላለን፡፡ 

1/ከመጽሐፉ ከገጽ 8 የተወሰደ ፦
‹‹አነ ውእቱ ፍኖትኒ ወጽድቅኒ ወሕይወትኒ አልቦ ዘይመጽእ ኀበ አብ ዘእንበለ እንተ ኀቤየ ›› ማለትም ‹‹እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ››በማለቱ በእርሱ መንገድነት ካልሆነ በቀር በሌሎች  መንገዶች ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የማይቻል መሆኑን አረጋግጧል/ዮሐ.14፤6 እዚህ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ‹‹መንገድ›› ብሎ ጠርቷል፤መንገድ በመንገደኛውና መንገደኛው በሚደርስበት ቦታ መካከል የተዘረጋ እንደሆነ ሁሉ ክርስቶስም ሰማያዊ መንገደኞች በሆንነው በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ያለ መካከለኛ ነው፡፡ ከእርሱም በቀር ሌላ መካከለኛ የለም፡፡›› በማለት ጽፈዋል፡፡
ከዚህ በላይ ያስነበብናችሁ ከመጽሐፋቸው ቃል በቃል የተወሰደ ሲሆን ሃሳቡን ጠቅለል በማድረግ በሁለት ከፍለን እናየዋለን፡፡ ይኸውም ፦
     ሀ/ ሐሰታቸውን እውነት ለማስመሰል የተጠቀሙበትን የግዕዙን ጥቅስ ከትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱስ አምጥተን፤ 
     ለ /‹‹መንገድ›› የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ያለውን ትርጉም የተወሰኑ ጥቅሶችን መሰረት አድርገን  እንመለከተዋለን፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነገር ሁሉ ማስተዋሉን ይስጠን፡፡