Saturday, August 19, 2017

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ፡፡” ማቴ.7፤16 ክፍል ሰላሳ ሦስት

ከክፍል ሰላሳ ሁለት የቀጠለ፦
የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ?  
ለዚህ ዕለት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
     የተከበራችሁ አንባብያን በክፍል ሰላሳ ሁለት  "በቀጣይ ጽሁፋችን እነዚሁ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን / ተሐድሶ ተብዬዎቹ/ እውነተኛ መስሎ ለማሳሳት የሚጠቀሙባቸውን ዋና ዋና ስልቶች በመጠኑ እንዳስሳለን፡፡ "ብለን በይደር አቆይተነው እንደነበር ይታወሳል፡፡አሁንም ይህ የቤት ሥራችን እንዳለ ሆኖ ለዛሬው "አዘክሪ ድንግል"በሚል ርዕስ እመቤታችንን የምንማጸንበት ወቅታዊ መልእክት  አቅርበንላችኋል፡፡
መልካም በዓል፡፡

Wednesday, August 9, 2017

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ፡፡” ማቴ.7፤16 ክፍል ሰላሳ ሁለት

ከክፍል ሰላሳ አንድ የቀጠለ፦

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ?

ለዚህ ዕለት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡

"በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ"ማቴ.13፥34

       ለስሙ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣበት አንዱና ዋነኛው ዓላማ የአዳምን ዘር ከወደቀበት ለማንሳት፣ ማለትም በኃጢአቱ ምክንያት ከተፈረደበት ሞት ለማዳን ስለሆነ፤ ማንም ፍጡር ሊሳተፍበት በማይችለው የቤዛነት ሥራው አዳምን ከነልጅ ልጆቹ ከሞት ወደ ሕይወት አሸጋግሮናል፡፡ መለኪያ ለሌለው ለዚህ ፍቅሩ ምስጋና ይግባውና፤ ሁለተኛው ዓላማ ደግሞ በአርአያነት ተግባሩ እኛም እንድንከተለው ምሳሌ ሆኖ ለማሳየት ነው፡፡

Tuesday, August 8, 2017

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ፡፡” ማቴ.7፤16 ክፍል ሰላሳ አንድ

ከክፍል ሰላሳ የቀጠለ፦

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ?

ለዚህ ዕለት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡

      ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ምዕ.12 ቁጥር 9  “ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ” ብሎ ባስተማረን መሠረት፤ዓላማችን አንድ እስከሆነ ድረስ፤ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትና ሥርዓት ጠብቀው የሚያስተምሩትን የተለያዩ መምህራንን ትምህርቶች፤በዚች የመወያያ ጦማር ላይ እንድታነቡ ስናደርግ እንደነበረ እናስታውሳለን፡፡
     ዛሬ በዚች ክፍል የምናስነብባችሁ "ማቴዎስ ናታኒም" የተባሉ ወንድማችን በማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ "ነገረ ክርስቶስ በገድላት" በሚል ርዕስ ያስተላለፉትን ጠቃሚ ትምህርት ነው፡፡የመልእክቱ ይዘት  ለእኛ ለተዋሕዶ ልጆች ትምህርት፤ እንዲሁም ሳይገባቸውና ሳይገባቸው (" "ጠብቆ ይነበብ) ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ለሚተቹ ደግሞ ምላሽ የሚሰጥ ስለሆነ ሁላችን አንብበን እንድንጠቀምበት ማስተዋሉን ያድለን፡፡
ጽሁፉን ለንባብ እንዲመች ከማድረግና አንዳንድ የፊደላት እርማት ከማድረግ በስተቀር የራሳችንን ሃሳብ አልጨመርንም፡፡

Wednesday, August 2, 2017

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ፡፡” ማቴ.7፤16 ክፍል ሰላሳ


ከክፍል ሃያ ዘጠኝ የቀጠለ

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ?

ለዚህ ዕለት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡

    ሁላችንም እንደምናውቀው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሳይሆኑ መስለውና ተመሳስለው የተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ዶግማ፣ሥርዓትና ትውፊቷን የራሳቸው ልብ ወለድ በሆነ እንግዳ ትምህርት ለመለወጥና በመጨረሻም የፕሮቴስታንት ጥገኛ ለማድረግ የጥፋት ተልእኳቸውን  ተግተው በመፈጸም ላይ የሚገኙ፤ እራሳቸውን "ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ" ብለው የሚጠሩ ክፍሎች ቤ/ክንን ምን ያህል እተፈታተኗት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
      ይህንኑ የክህደት ሥራቸውን ሳያፍሩና ሳይፈሩ "ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ"  ብለው ባለ 43 ገጽ ክህደት መግለጫ ሲያወጡ፤እኛም "በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ…"/1ኛ ጴጥ.3፥15/ በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት፤ ቅዱሳን አባቶች ተገቢውን መልስ እስከሚሰጡ ድረስ ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልምና በዚሁ ድረ-ገጻችን ( ወልድ ዋሕድ) ላይ በክፍል 19፣22፣23፣24 መልስ መስጠታችን ይታወሳል፡፡
       ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባውና የቤተ ክርስቲያናችን የሊቃውንት ጉባኤ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ከላይ ለተጠቀሰው የክህደት መግለጫቸው "ከውሾችና ከክፉ አድራጊዎች ተጠበቁ"(ፊል. ፫፥፪ ) በሚል ርዕስ ተገቢው ምላሽ ስለተሰጠ፤ አባቶቻችን ብዙ ደክመው ያዘጋጁት መጸሐፍ ሁላችንም የተዋህዶ ልጆች በመግዛትና በጥሞና በመመልከት  እራሳችንንም ሆነ ሌሎችን ከስህተት ትምህርት በመጠበቅ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን መወጣት ይገባናል፡፡

የመጽሐፉ የፊት ገጽታ
"ከውሾችና ከክፉ አድራጊዎች ተጠበቁ"
(ፊል.፫፥፪)
"ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ"
ለሚለው የመናፍቃን አስመሳይ መግለጫ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የተሰጠ መልስ
በሊቃውንት ጉባኤ ተዘጋጅቶ በትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት አሳታሚነት ታተመ
                                                                                    ጥር ፳፻ወ፱

                                                                                     አዲስ አበባ