ከክፍል ሃያ ዘጠኝ የቀጠለ
የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ?
ለዚህ ዕለት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
ሁላችንም
እንደምናውቀው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሳይሆኑ መስለውና ተመሳስለው የተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ዶግማ፣ሥርዓትና ትውፊቷን
የራሳቸው ልብ ወለድ በሆነ እንግዳ ትምህርት ለመለወጥና በመጨረሻም የፕሮቴስታንት ጥገኛ ለማድረግ የጥፋት ተልእኳቸውን ተግተው በመፈጸም ላይ የሚገኙ፤ እራሳቸውን "ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ" ብለው የሚጠሩ ክፍሎች ቤ/ክንን ምን ያህል እተፈታተኗት እንደሆነ ግልጽ
ነው፡፡
ይህንኑ የክህደት ሥራቸውን ሳያፍሩና ሳይፈሩ "ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ" ብለው ባለ 43 ገጽ ክህደት መግለጫ ሲያወጡ፤እኛም "በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ
ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ…"/1ኛ ጴጥ.3፥15/ በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት፤ ቅዱሳን አባቶች ተገቢውን መልስ እስከሚሰጡ ድረስ ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልምና በዚሁ ድረ-ገጻችን ( ወልድ ዋሕድ) ላይ በክፍል 19፣22፣23፣24 መልስ መስጠታችን ይታወሳል፡፡
ለእግዚአብሔር
ክብር ምስጋና ይግባውና የቤተ ክርስቲያናችን የሊቃውንት ጉባኤ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ከላይ ለተጠቀሰው የክህደት መግለጫቸው "ከውሾችና ከክፉ አድራጊዎች ተጠበቁ"(ፊል. ፫፥፪ ) በሚል ርዕስ ተገቢው ምላሽ ስለተሰጠ፤
አባቶቻችን ብዙ ደክመው ያዘጋጁት መጸሐፍ ሁላችንም የተዋህዶ ልጆች በመግዛትና በጥሞና በመመልከት እራሳችንንም ሆነ ሌሎችን ከስህተት ትምህርት በመጠበቅ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን
መወጣት ይገባናል፡፡
የመጽሐፉ የፊት ገጽታ
"ከውሾችና ከክፉ አድራጊዎች ተጠበቁ"
(ፊል.፫፥፪)
"ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ"
ለሚለው የመናፍቃን አስመሳይ መግለጫ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የተሰጠ መልስ
በሊቃውንት ጉባኤ ተዘጋጅቶ በትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት አሳታሚነት ታተመ
ጥር ፳፻ወ፱
አዲስ አበባ